October 22, 2020

Central Gondar Communication

10h  · 

በሰሜን አሜሪካና ጀርመን ሀገር ከሚኖሩ የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት እንዲሁም የጎንደር ልማት ማህበር የአንድ መቶ ኩንታል በቆሎ ድጋፍ አደረጉ።

ጥቅምት 12/2013 የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ

በሰሜን አሜሪካና ጀርመን ሀገር ከሚኖሩ የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት እንዲሁም የጎንደር ልማት ማህበር የመቶ ኩንታል በቆሎ ድጋፍ ማድረጋቸውን የህብረቱ ተወካይ የሆኑት አቶ አምላኩ ነጋሽ ተናግረዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ ደንቢያ በጎርፍ ለተፈናቀሉ ወገኖች መሆኑን አስረድተዋል።

አቶ አምላኩ ነጋሽ ጨምረው አንደገለፁት ህብረቱ የወገን ደራሽነቱን ያሳየበት ተግባር ሲሆን በዚህ በያዝነው ወር በተመሳሳይ መልኩ ለደቡብ ጎንደር ዞን በጎርፍ ለተፈናቀሉ ወገኖች 176 ኩንታል ድጋፍ ማድረጋቸውን አብራርተዋል።

በርክክብ ስነ-ስርዓቱ የተገኙት የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ተወካይ አቶ እምቢአለ ታረቀኝ በበኩላቸው ለወገን ደራሽ ወገን ነውና የተሰጠውን እርዳታ በተፈናቃዮች ስም ከልብ እያመሰገን ሌሎች ወገኖችም አስፈላጊውን ድጋፍ እንድታደርጉልን ጥሪያችን እናቀርባለን ብለዋል።

የጎንደር ህብረት ከአሁን በፊት በጭልጋና አካባቢው በተፈጠረው ግጭት ለተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ ማድረጋቸውን አቶ እምቢአለ ታረቀኝ አንስተው ድርጅቱ ሁሌም ከጎናች መሆኑን አሳይቶናል ብለዋል።

በዋኘው አዳነ

ጎንደር ሕብረት በጎርፍ ለተጎዱ እርዳታ ላክ

​መስከረም 25፣ 2020

ጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ስሜን አሜሪካና ጀርመን በጎርፍ የተነሳ ክብቶቻቸው በጎርፍ ለተወስዱያ፤ ንብረታቸው ፤ስብላቸውንና ቤቶቻቸው በውሀ ለተጥለቀለቁ  የደራ፤ ፎገራ ፤ሊቦ ክምከም እንዲሁም ደንቢያ ወረዳዎቸ የገንዝብ ማሰባሰብ ካካሄደ በኋል $10000 ( 350 000 ብር ልኳል፡ ፡የምጋብ  እርዳታ ስርጭቱን  የጎንደር ቻፕተር በጎንደር ከተማ ክጎልማና  ክአደጋ መክላከልና የምግብ አቅርቦት ተወካዮች ጋር  በመተባበር በደራ፤ሊቦ ክምክምና ፎገራ ወረዳዎችያብረከተ ሲሆን በቅርቡ ደጎሞ እርዳታውን ለደንቢያ ወረዳ ያበርክታል፡፡ 

South Gondar Zone Communication

October 15 at 2:42 PM  · 

በደቡብ ጎንደር እስተዳደር ዞን በፎገራ፣ ሊቦ እና ደራ ወረዳወች በጣና ወደኋላ መመለስ መክንያት ጉዳት ለደረሰባቸውን አርሶ አደሮች 176.7 ኩንታል በቆሎ ድጋፍ ተደረገላቸው፡፡

የደቡብ ጎንደር እስተዳደር ዞን አደጋ መከላከልእና ምግብዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አገኘሁ ዳኛው በሶስቱ ወረዳወች በ7 ቀበሌወች በጣና ወደኋላ መመለስ ምክንያት ከመኖሪያ አካባቢያቸው ለተፈናቀሉ አርሶ አደሮች ከተለያዩ ረጅ ድርጅቶች፣ማህበራት እና ባለሃብቶች ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ ጠቁመው በእለቱ ከስሜን አሜሪካ እና በጀርመን አገር የሚኖሩ የጎንደር ህብረት እና የጎንደር መልሶ ማቋቋምና ልማት ማህበር አባላት 176.7 ኩንታል በቆሎ ድጋፍ መደረጉን አስመልክቶ በዞኑ ተጎጅ አርሶ አደሮች ስም የላቀ ምስጋና አቅርበዋል ፡፡

አቶ አገኘሁ አክለውም እነዚህን አርሶ አደሮች በዘላቂነት ለማቋቋም ውሃው እየሸሸ ሲሄድ የተለቀቀውን ማሳ በተተኪ ዘር እየሸፈኑ ምርት እንዲያመርቱ አሁን ላይ ሰፊ የሆነ ቅንጅታዊ ስራ የሚጠይቀው ከ 8ሽህ 500 ኩንታል በላይ ተተኪ ዘር በተገቢው መንገድ እንዲቀርብ ማድረግ ነው፡፡ከዚህ ጎን ለጎን እንደ የውሃ ፣ትምህርት፣ ጤና እና መሰል ተቋማት እንዲሟሉ በማድረግ ወደ ቀያቸው የመመለስ ስራ በቅንጀት መስራት እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የደቡብ ጎንደር መልሶ ማቋቋምና ልማት ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ሞላ እንግዳ በእርክክቡ ላይ ተገኝተው ማህበሩ በስሜን አሜሪካ እና በጀርመን አገር የሚኖሩ የጎንደር ህብረት ማህበር ጋር በመቀናጀት ከዚህ ቀደም የኮሮና ውረርሽኝን ለመከላከል ለ5ቱ ዞኖች 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት ዘይት እና የፊኖ ዱቄት ድጋፍ እንዳደረገ ጠቁመው በእለቱ 176.7 ኩንታል በቆሎ በጎንደር ከተማ የጎንደር ህበረት ኮሚቴ ጸሀፊ ከወጣት ምህረት አምሳሉ እና ሆነልኝ አበበ ጋር አስረክበዋል፡፡

ወጣት ምህረት አምሳሉ እና ሆነልኝ አበበ ማህበሩ ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢወች እለታዊ ድጋፍ የማድረግ ስራ ሲሰራ እንደቆየ ጠቁመው በቀጣይ መሰረቱን ጎንደር ላይ በማድረግ አገር በቀል መንግስታዊ ያለሆነ ተቋም ሁኖ በዞኑ ያሉ ችግሮችን በመለየት ችግር ፈች በሆኑ መሰረተ ልማቶች ላይ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

በእርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አወቀ ዘመነ የጎንደር ህብረት በአሜሪካ እና ጀርመን አገር የሚኖሩ ተወላጆች ከዚህ በፊት የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ከ300 ሽህ ብር በላይ ወጭ በማድረግ 300 ኩንታል ፊኖ ዱቄት እና 517 ሊትር ዘይት ለችግር ለተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡

እንዲሁም የእርብ እና የጉማራ ወንዞች የክረምት የጎርፍ ውሀ የመሸከም አቅማቸው እንዲያድግ ዞኑና የክልሉ መንግስት በቅንጅት ባደረገው ጥረት ውጤት ያስገኘ እንደሆነ ጠቁመው የጣናን ወደኋላ መመለስ ተከትሎ በደራ ፣ፎገራ እና ሊቦ ከምከም ወረዳዎች ጉዳት የደረሰ በመሆኑ ህብረተሰቡን ለማገዝ በሚደረገው ጥረት ገንዘብ በማሰባሰብ በ220 ሽህ 885 ብር 176.7 ኩንታል ለምግብነት የሚውል በቆሎ በዛሬው እለት አስረክበውናል፡፡ በመሆኑም ድጋፉን ላደረሱት እና ገንዘቡን ለለገሱ ሁሉ በዞኑ ስም የላቀ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት

ጥቅምት 06/2013 ዓ/ም

ዘጋቢ፣ምህረት አለሙ

May 16, 2020

Part I
The Livelihood’s that Egypt Robbed and the Conflicts It Perpetuates Aklog Birara (Dr)

Egyptian Misrepresentation of History Perpetuates Ethiopia’s Poverty
History teaches us that about 45...

May 6, 2020

ሚያዚያ 28 2012 (5/5/2020)
 
የወሰኑ ጉዳይ
“የነገር ትህትና ያስረታል፣ የበትር ትህትና ያስመታል”
ከሱዳን ጋር ያለው የወሰናችን ጉዳይ ዛሬም እንደትናንትናው እና እንደዚያ ቀደሙ ያለ እልባት ተንጠልጥሎ ቆይቶ የግጭት አፋፍ ላይ አድርሶናል። ባለፉት ሁለት ወራት የሱዳን የመከላከያ ሠራዊት በኢትዮ...

April 27, 2020

በተለያዩ ውጥረቶች ውስጥ የኖረችው ጎንደር ለየት ያለ ዜና ይዛ ተሰምታለች። ሁሉም እንደሚያውቀው ከውጥረት ወደ ውጥረት ስትረማመድና የመሻኮችያ፣ የሴራ፣ የቀውስ መናሃሪያ ሆኖ ቆይታለች። ይህ ብቻ አይደለም የእነ አይበገሬ አገርም ሆና ስትታገል ኖራለች። በቅርቡም ያ የተለመደው ቀውስ ተከስቶባት በ የካቲትና...

April 14, 2020


የጎንደር ሕብረት የኮረና ቫይረስን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት
አንድ ሚሊዮን ተኩል የኢትዮጵያ ብር መደበ
እንደምታውቁት የኮረና ቫይረስ ሁሉንም አገራት እያዳረሰ ነው። ባገራችን መግባቱን የማያውቅ አለ ብለን አናምንም። ባህላችንም ሆነ ጥብቅ የእምነት ስነስርአቶቻችን ለበሽታው መዛመት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራሉ።...

April 12, 2020

                               
...

April 1, 2020

መጋቢት 23 2012 (04/01/2020)
 
‘ሊጣላ የመጣ፣ ሰበብ አያጣ’
በሰሞኑ በጎንደርና በዙሪያዋ ተከታትለው እየደረሱ ያሉ አጠያያቂ ጉዳዮች የፌደራሉ፣ የክልሉንና ሌላንም ክልል ያካተተ ጉዳይ በሚመስል ሁኔታ እየተካሄዱ ናቸው። እንደሚታወቀው በጎንደርና በዙሪያዋ ሆነው የማያውቁ፣ ከታሪኩና ከባህሉ የራቁ...

November 6, 2019

መቸንከሪያ መሃል እያጣን ነው

ድሮ አባቶቻችን ዳር ድንበር ሲደፈር፣ ጦራቸውን ሰብቀው ጋሻቸውን አንግበው ወደ ተደፈረው ድንበር ይተማሉ፡፡ ዳር ሲደፈር፣ መሃል ዳር ይሆናል ይሉ ነበር፡፡ ዛሬ በአገራችን የሕግ የበላይነት በመጥፋቱ የሩቁ፣ የዳር ዳሩና የመሓሉ የሚባል የለም፡፡ የዘር የሃይማኖትና የቋንቋን ልዩነ...

October 22, 2019

የመንግሥት ተቀዳሚ ተግባሩ፣ የሕዝብን ደህንነትና ፀጥታ ማስጠበቅ፣ ሕግና ስነስርአት ማስከበር እና ፍትህ እንዲሰፍን ማድረግ ነው። እነዚህን ለመተግበር የመንግሥት አውታሮች አመች ሆነው መዋቀር ይገባቸዋል። በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የአገሪቱ አመራር አካሎች፣ የፖሊስ ኃይሉንና ፍርድ ቤቶቹን ጨምሮ የግለሰብን መ...

October 3, 2019

       

መስከረም 20 2012 ዓ. ም. (10/01/2019)

‘አንድ እርምጃ ወደፊት፣ ሁለት እርምጃ ወደ ኋላ’

የቅማንት ማንነት ጥያቄ በሚል በወያኔ ተጠንሰሶ፣ በአማራው ክልል ውስጥ በሰገሰጓቸው አቀንቃኞች ተላላኪነት በተለያየ መንገድ ማሕበረሰብን ከማሕበረ ሰ...

Please reload

Thank you for your generous support. Our ability to proomot economic  and  soical justice in  Ethiopia depends  on your support. 
 

Please support Gonder Hibret

  • Facebook Classic
  • Twitter Classic
  • Google Classic

ሰላም  ሁኝ ጎንደር፣ ታምራት ሞላ

  • s-facebook
  • Twitter Metallic
  • s-linkedin