Search
  • gyisma83

ከወረወረ የመከረ

  1. 4126 Deerwood Trail, Eagan MN 55122Tel 651 808 3300የካቲት 11 2012 (03/19/2020)

ከወረወረ የመከረ

በሰሞኑ ከነፈሱት ዜናዎች ገኖ በመወራት ላይ ያለው በጎንደር፣ በገጠሩና በከተማው ሥርዓት አልበኝነት ነግሶ፣ የሕዝቡን ጸጥታ እንዳደፈረሰ እና ዘረፋዎች፣ አልፎ አልፎም ግዲያዎች እንደተፈጸሙ ነው። ለዚህ ብልሹ ሁኔታ ተጠያቂዎች ብዙ ናቸው። የክልሉ መንግሥት ጸጥታ ለማስከበር አልቻለም። ለዚህም አንደኛው ዋና ምክንያት ባለፉት ሃያ ሰባት (27) ዓመታት ከስርአቱ ጋር ወግነው የኖሩ፣ ነገን የሚሰጉ በየእርከኑ ተሰግስገው የሚገኙ የኢ ህ አ ዴ ግ ባለሥልጣኖች ናቸው። ሌላው የድርጅቶችን ስም እንደ ለምድ ለብሰው ሰላማዊውን ሰው የሚያድኑ ወንጀለኞች ናቸው። ሌሎቹ ደግሞ በግለሰብ ከተሜውንም ሆነ አርሶ አደሩን ያስጨነቁ በረት ሰባሪዎችና ወንበዴዎች ናቸው። በጣም የሚያሳስበው እነዚህ ሁሉ ከሌሎች የውጭ ሃይሎች ጋር ያላቸው የማይናቅ ትስስር ነው።

እርግጥ ነው፤ መንግሥት ጸጥታውን ያስጠብቅ እያልን ስንጮህ ከርመናል። ይህን ስንል መንግሥት ሁኔታውን ለመቆጣጠር በጥፋተኞች ላይ እርምጃ ይውሰድ፣ ከሕዝቡ ጋር ይምከር፣ የአገር ሽማግሌዎችንና የሃይማኖት አባቶች በማሳተፍ ዘላቂ መፍትሄ ይስጥ ለማለት ነበር። ሆኖም ግን ባለፉት ሁለት ቀናት እነዚህን እርምጃዎች ለመውሰድ ከዓመት በላይ ያመናታ መንግሥት ዛሬ ብድግ ብሎ ለውጡን ለማምጣት ትልቅ መስእዋትነት የከፈሉትን ግለሰቦችን እና ሕዝብ ሠራዊት አጓጉዞ፣ እርሻቸው ድረስ ሄዶ፣ ተኩስ ከፍቶ ለብዙዎች መቁሰልና መሞት ምክንያት ሆኗል። ይህ ድርጊት ሌላ ዓላማን ያዘለ ከሌሎች የፖለቲካ ጥያቄዎች ጋር የተሳሰረ መሆኑን ማንም እንደማይስተው ግልጽ ሊሆን ይገባል። የዚህ ጦስ ወደፊት ማስከፈሉ እንደማይቀር አጥብቀን ማሳሰብ እንወዳለን።

በከተሞቻችን ጸጥታውን አደፍርሰዋል በሚባሉ ግለሰቦችና ቡድኖች ላይ የሚወሰደው እርምጃ አግባብ ያለው እንዲሆን የጅምላ የሃይል እርምጃ ከመውሰድ መንግሥት እንዲቆጠብ እንጠይቃለን።

በመጨረሻም የምናሳስበው

1ኛ/ የክልሉ መንግሥት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች ምሁራንና ወጣቶች የሚሳተፉበት የሰላም ጉባዔ እንዲካሂድ።

2ኛ/ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ተሰግስገው ሰላም እንዳይኖር የሚሰሩ የመንግሥት ባለስልጣኖች ተለቅመው እንዲወጡ።

3ኛ/ ዘላቂ መፍትሄ የሚገኘው ሕዝብ የራሱን ወኪል ሲመርጥ ነውና ሕዝቡ ይህን መብቱን እንዲያገኝ ነው።

የጎንደር ሕዝብ የተጫኑበትን ተጽእኖዎች ሰብሮ ይወጣል።

0 views
  • s-facebook
  • Twitter Metallic
  • s-linkedin