Search
  • Abebe Gelagay

ይድረስ ለትግራይ ሕዝብ!


በመቀሌና በአዲግራት ዩኒቨርስቲዎች የትግርኛ ተናጋሪ ባልሆኑ በተለይም ደግሞ በአማራ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ እየተወሰደ ያለውን ለመስማት የሚከብድ አሰቃቂ ግድያና ድብደባ በመስማታችን በሟቾች የፎቶግራፍ ማስረጃ ጭምር በማረጋገጣችን እጅግ ከፍተኛ ሐዘን ተስምቶናል። የሐዘናችን ጥልቀትም ለሞቱትና ለተደበደቡት፤ አካለ ጎደሎ ለሆኑት ተማሪዎች ብቻ አይደለም። ሐዘናችን ለትግራይ ሕዝብ የወደፊት እጣ ፈንታም ጭምር እንጂ

በኢትዮጵያዊነቱና በሐይማኖቱ ታማኛና ጽኑ ከሚባለው የትግራይ ሕዝብ ውስጥ ከአርባ ዓመት በፊት የተፈለፈለው አናሳ የወያኔ ቡድን ሥልጣን ከመያዙ ማግሥት ጀምሮ ኢትዮጵያ አገራችንን በጎሳ ሸንሽኖ የዘረኝነት መርዝ እየጋተ ያሳደጋቸው የትግራይ ወጣቶችና ተመሳሳይ የዘረኝነት ልክፍት የተጠናወታቸው አዋቂዎች ጭምር እጅግ ኋላ ቀር በሆነ ወገን ወገኑን የመብላት የእንሰሳት ባህሪና ተግባር ላይ ተነክረው በማየታችን፤ የሚያስከፍለውንም እጅግ ከባድ ዋጋም ከወዲሁ በማየታችን ኃዘናችንን እጥፍ ድርብ አድርጎታል። የትግራይ ሕዝብ በኢትዮጵያ ውስጥ ከጠረፍ እስከ ጠረፍ ድሮም ሆነ ዛሬ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ተከብሮ ኖሯል። አሁን ግን በክልሉ ውስጥ እየተፈጸመ ላለው አረመኒያዊ ወንጀል ምንም አይነት ተቃውሞ አለማሰማቱ ለሚመጣው አጸፋ እራሱን እያጋለጠ፤ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እየተቆራረጠ እንደሆነ ሊረዳው ይገባ ነበር። በችግርና በእርዛት ወልደው አሳድገው፤ በተሻለ የእውቀት ማእረግ ተመርቆ ያሳልፍልኛል ብለው በክልላችሁ ወደሚገኙት ዩኒቨርስቲዎች የላኳቸውን ለግላጋ ልጆች ገድላችሁ የወላድን ልብ በሚሰብር ሁኔታ ሬሳቸውን ስትልኩላቸው ከንፈር መጠው፤ እምባ አፍሰው አንገት ደፍተው የሚያልፉት ተግባር አለመሆኑን አልተረዳችሁም፤ ወይም ትዕቢታችሁ ጣራ ነክቷል። ኢትዮጵያውያን በዘመናት ፍልሰት አንዱ ወደ አንዱ አካባቢ እየተዘዋወረ የሰፈረ ወንድማማች፤ አንድ ባህሪ ወይም ወኔ ያለው ሕዝብ

በመሆኑ፤ ዛሬ ልጆቹ በግፍ የተገደሉበት ነገ ደሙን ከማን ላይ እንደሚመልስ፤ እናንተም የምታጡት አይመስለንም። ምናልባት የወያኔን መንግሥት መከታ በማድረግ ከሆነ በጣም ተሳስታችኋል። የወያኔ ቀኑ እየመሸ ከ11ኛው ሰዓት ላይ ደርሷል። እንኳን የትግራይን ሕዝብ እራሱን ለማዳን አይችልም። ወያኔ እንደማንኛውም ዘመናቸውን ቆጥረው እንዳለፉ መንግሥታት ነገ ከነገ ወዲያ ይሄዳል፤ የትግራይ ሕዝብ ግን ከሌላው ወገኑ ጋር ቀሪ ነው። ታዲያ ከዚያም ቤት እሳት አለ ብሎ አርቆ ማሰብ አለመቻሉ ከምን አንጻር ይሆን? ትግራይ ብዙ ምሁራንና ሽማግሌዎች ያሉባት ክ/ሀገር ናት። ይሁን እንጅ እየመጣ ያለውን አደጋ ቆም ብሎ አለማየት ለምን ይሆን? የሌላን ጎሳ እንደጠላት ፈርጆ መነሳት ለአገራችንም ለሕዝባችንም ጥሮ እንዳልሆነ የትግራይ ሙሁራን ሊገነዝቡት በተገባ ነበር። በሩዋንዳና በሌሎች አገሮች የደረሰው የዘር ጥፋት በዚሁ ዓይነት መንግሥትን መከታ በማድረግ የተጀመረና የተፈጸመ አሰቃቂና በዓለም አስከፊ ምዕራፍን የያዘ ፍጅት ነው። እንደሚባለው ወያኔ ዘላለማዊ ገዥ ሆኖ ይኖራል ብላችሁ አስባችሁ ከሆነ እጅግ የተሳሳተ ጎዳና እየተከተላችሁ ነው። እስከ አሁን ድረስ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔን ከትግራይ ሕዝብ ለይቶ ለማየት ሲታገል ቆይቶ ነበር። አሁን ግን ይህን ተስፋውን በልጆቹ ደም አቅልማችሁ አጨለማችሁት!! ልቡንም አደማችሁት! የኢትዮጵያ ሕዝብ ይጠብቅ የነበረውን የተቃውሞ ድጋፍ ከወያኔ ጎን እንደቆማችሁ በሚያረጋግጥ መልኩ ከአብራኩ የወጡትን በእምነት ወገኖቸ ብሎ በክልላችሁ እንዲማሩ በአደራ የላከላቸሁን ልጆቹን በላችሁበት። አሁንም እየሞላ ያለው የእዳው መስፈሪያ ሞልቶ ከመፍሰሱ በፊት ዘርን መሰረት ያደረገ ግድያ፤ ጥላቻ እንዲቆም እና የሕዝብ አመኔታ እንድታገኙ ወደ ድሮው ክቡር ወደሆነው ኢትዮጵያዊነት ፍቅራችሁ ትመለሱ ዘንድ የጎንደር ሕብረት ጥሪውን ያስተላልፋል። ቢያንስ በክልላችሁ ውስጥ እየተፈጸመ ያለውን ግድያና ድብደባ አስቁሙ፤ እናንተም ከጥፋት ትብብር ታቀቡ። በሰላም ትምህርት ለመቅሰም ከተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎችን ከነህይወታቸው ወደመጡበት እንዲመለሱ ተባበሩ። ወላጆች ልጆቻችሁን ስላማዊና ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር አብሮ ለመኖር ዝግጁ እንዲሆኑ ምከሩ።

በአጠቃላይ በወያኔ የዘር ፖለቲካ ምክንያት እየመጣ ያለውን አሰፈሪ ሁኔት በመገንዝብ ጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት፤ የኢትዮጵያ ልእዋላዊነት፤ የሕዝባችን ሰላም እና አንድነት የሚያሳስባችሁ ወገኖች ስብስቦችና የፖለቲካ ድርጅቶች ከመቸውም በላይ ልዩነትን ወደ ጎን በመተው በጋራ በመቆም ከወያኔ የጥፋት ጎንዳና ሕዝባችንና አገራችን እንታደግ ዘንድ የዘወትር ጥሪውን ያቀርባል። በትግራም ሆነ በሌላ አካባቢ በዘር ምክንያት ህይዎታቸው ላለፈ ቤተሰቦች መጽናናትን እንመኛለን! ኢትዮጵያን ከጎሳ ፍጅት እናድናት!!!

ጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት

ጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት 12/12/17


337 views
  • s-facebook
  • Twitter Metallic
  • s-linkedin