Search
  • Abebe Gelagay

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጫካ አውሬ ምንም አይጠብቅም!


ወያኔ ካለፈው ስህተቱ የማይማር፤ በበደለው የማይጸፀት ሁለት እግር ያለው የጫካ አውሬ ነው ብንል ፈጽሞ አልተሳሳትነም። ሃያ ስምንት ዓመት በሥልጣን፤ አሥራ ሰባት አመት በጫካ፤ በድምሩ አርባ አምስት ዓመታትን ያስቆጠረው ከአንድ ብሔር የተኮለኮለ አናሳ ጥርቅም ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ የራሱን ጓዶቹን በጭካኔ እየረሸነ የአውሬነት ባህሪውን እንደያዘ ምኒሊክ ቤተ መንግሥት ድረስ ዘልቆ ከገባ ጊዜ ጀምሮም ቢሆን ትንሽም እንኳ ራሱን ማየት ባለመቻሉ ዛሬም ገና ሲፈጠር የተሸከመውን ጠመንጃ ከትክሻው ሊያወርድ አልቻለም። የሰውንም ህይወት ማጥፋት ዶሮ እንኳ የገደለ አይመሥለውም።

በዚህ አረመኔ መንግሥት በምርጫ ሰበብ የጠፋውን ህይወት እንኳ ሳናስብ በሳለፍናቸው ሁለት ዓመቶች ብቻ፤ በኢሪቻ በዓል፤ የዲሞክራሲ መብታቸው እንዲከበርላቸው እጅ ከማውለብለብ፤ ድምፅ ከማሰማት በቀር ምንም አይነት ጎጂ መሳሪያ ባላነገቡ የኦሮሞ ወገኖቻችን፤ የጎነደር፤ የጎጃም እና የደቡብ ወገኖቻችን ላይ የፈፀመው ጭፍጨፋ፤ የወለዱ እናቶችን ልብ የሚሰብር፤ ያለወለዱትን እህቶች ማህፀን የሚያደርቅ እጅግ አሰቃቂ ዘመን የማይሽረው፤ አንደበት ይቅር የማይለው አረመኔያዊ ታሪክ ፈፅሟል። ወያኔ አሁንም አውሬ ነው!! አውሬ እንደ ሰው አያስብም፤ ባህልም፤ ኃይማኖትም፤ ሰባዓዊ ፍቅርም የለውም። በመሆኑም በዘንድሮው የኦሮቶዶክስ ተዋኅዶ ዕምነት በሚከበርበት የጥምቀት በዓል ላይ እግዚአብሔርን ሳይፈራ በአሰቃቂ ሁኔታ ሴት፤ ወንድ፤ ህፃን ሽማግሌ ሳይለይ በጅምላ ብዛት ያላቸው የወልድያ ወገኖቻችንን ጨፍጭፏል

እግዚአብሔርን ታቦት አጅበው ሥራዓተ ጥምቀቱን አክብረው፤ በደስታና በፈንጠዝያ እንደ ድሮው ቤታቸው ተመልሰው ሊዝናኑ፤ ቤተ ዘመድ፤ ጓደኛ ሊያስተናግዱ የጋበዙ እናቶች በድንገት በወያኔ በደረሰባቸው ጭፍጨፋ ልጆቻቸውን በሞት ተነጥቀው በእንባ ታጥበዋል። የዘለዓለም ኃዘን ልባቸውን ሰንጥቆ የማይጠግን የሸክላ ስባሪ አድርጎታል! በወያኔ ሥራዓት የክብር በዓል ወይም አውደ ዓመት ሲመጣ የሞትን ድባብ ይዞ እንደሚመጣ በኢትዮጵያውያን ስነ ልቦና ሰርጾ ገብቷል።

ባንጻሩ ግን አገር ሲደፈር ወገን ሲበደል እምቢ አሻፈረኝ ባዩ ከቀን ወደቀን እየተጠናከረ መምጣቱ ምንም ባያጠራጥረንም፤ ሰላም፤ ፍቅርና አንድነት ሰባኪዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በአፍላ ጉልበታቸው፤ በለጋ እድሚያቸው ታቦት የሚያጅቡ፤ በድምፃቸው አምላካቸውን የሚያወድሱ ልጆቿን ከፊቷ ላይ በአረመኔው ወያኔ ጥይት እንደ ቅጠል ሲረግፉ እያየች ዝምታን መምረጧ ሌላው አሳፋሪ ታሪክ ነው። ይህ ደግሞ እኩል ከአረመኔው/ ከአውሬው ጎን ከመቆም ተለይቶ አይታይም። የዚህ ውጤት እጥር ባለ አማርኛ ሙታንን ሙታን ይቀበሯቸዋል እንጂ፤ ጨፍጫፊን የባረኩ ቀሳውስቶች፤ ሽጉጥና መስቀልን ሳይለዩ ያነገቱ ዘርፋፋ ቀሚስ ለባሾች እኩል ከወያኔ ጋር እንደሚፈረድባቸው ጥርጥር የለንም፤ ቀን ብቻ ነው እየተቆጠረ ያለው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ!

ከአንድ ብሔር የተጠራቀሙት አነስተኛ የወያኔ አውሬዎች ዘመን ተገባዶ እጅግ ጥቂት ጊዜ የቀረው የመጨረሻው ሰዓት ላይ መሆንህን በምታያቸው የወያኔ እንቅሥቃሴዎች ተረዳ። ወያኔ ድሮውንም ቢሆን በራሱ የማይተማመን፤ በእውነት ላይ ቆሞ ቀን ከሌት ወንጀልን በመፈፀም የጨለማ ተጓዥ ፈሪ ቡድን ቢሆንም፤ አሁን ግን ከመቸውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ የቀን ጨለማ እንደዋጠው የምታያቸው ምልክቶች ማረጋገጫ ይሁኑህ።

1. አንዱ ቡድን ህግ ሲያወጣ ሌላኛው ቡድ ይሽራል 2. ትናንት “እስካሁን ድረስ በድለናል፤ አጥፍተናል፤ ከአሁን በኋላ የፖለቲካ እሰርኞችን ፈትተን፤ የዲሞክራሲ ምሁዳሩን ቧ አድርገን እንከፍታለን” ያሉህ በኦሮምያ እና በወልድያ የደም ጎርፍ እረሸረሹልህ 3. አንዱ ቡድን እስረኛ ይፈታል ሲል፤ ሌላኛው ይፈታሉ ለተባሉት የቅድመ ሁኔታ ህግ ሲያረቅ ያድራል 4. አንደኛው ቡድን አትግደሉ ሲል፤ ሌላኛው ቡድን በጭካኔ ይጨፈጭፋል 5. አንዱ ቡድን ለተገደሉት ይቅርታ ሲጠይቅ፤ ሌላው ቡድን በጥፋታቸው ነው ብሎ ልብ ይልጣል 6. አንዱ ታድሰናል ሲል ሌላኛው በስብሶ ይታያል፤ ወዘተ..... በመሆኑም እኒህን እንደ ባቢሎዋውያን ቋንቋቸው የተደበላለቁ ጥርቅሞች መቸውንም ቢሆን ተችረው ለምትጠይቀው የሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ ምላሽ ይሰጡኛል፤ ለአገርና ለወገን ተችረው ስልጣን በሰላማዊ መንገንድ ይለቁልኛል ብለህ ለሰከንድ እንኳ አትዘናጋ።

ይልቁንም ትናንት የጎንደር እግር ኳስ ተጫዋቾች አድዋ ላይ በመደብደባቸው ተቆጭቶ ምላሽ የሰጠው የወልድያ ወገንህ ደሙ እንደ ጎርፍ ሲወርድ እያየህ፤ የጎንደር፤ የጎጃም፤ የሸዋ ዝምታ፤ እግርክን እየቆረጠመ ያለው አውሬ ራስህ ላይ እስኪደርስ እንደመጠበቅ ያስቆጥራል።

ድሮም ይሁን አሁን ለወያኔ እድሜ መራዘም፤ የወያኔ ጥንካሬ ሳይሆን የኛው አለመተባበር፤ አንዱ ሲጠቃ ሌላኛው በማድፈጥ፤ ተራ በተራ ለመቀጥቀጥ ስላመቸነው ብቻ ነው!! እናም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር ሆ!! ብሎ በመነሳት ይህን የመሸበት የጫካ አውሬ ለአንዴና ለመጨረሻ ከመላ ኢትዮጵያ አስወግዶ ሰላምና ዲሞክራሲን በማስከበር ልጆቻችን ቢከፋቸው ድምፃቸውን አሰምተው፤ ቢመቻቸው በሰላም ውለው የሚገቡባትን አገራቸውን ልናስከብር ግድ ይለናል። ስለዚህም የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔ እስከመጨረሻ የማይታመን፤ በቃሉ የማይቆም፤ ላወጣው ህግ የማይገዛ ድብልቅልቁ የወጣ የተደናበረ ቡድን መለሶ ከመጠናከሩ በፊት የተጀመረውን ሕዝባዊ ትግል የማንንም ኃይል ከውጭ ሳትጠብቅ የራስህን ታሪክ ሰሪነት እንድታስመሰክር በጋራ ትነሳ ዘንድ ጥሪውን ያስተላልፋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ መሪውን ከውስጡ በጭንቅ ይወልዳል እንጂ፤ ከውጭ አናጋጦ ጠብቆ አያውቅም!! በመግደል ለዘለዓለም የኖረ ማንም አምባ ገነን የለም! ወያኔም አይኖርም!!

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!

ጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት።


105 views
  • s-facebook
  • Twitter Metallic
  • s-linkedin