top of page

Empower
Growth

ህልውናችን በትግላችን ይረጋገጣል

ህልውናችን በትግላችን ይረጋገጣል!

ባለፉት ስድስት ዓመታት ኢትዮጵያ የሄደችበት የሰቆቃ ጉዞ ለማንም ግልፅ ነው። በሚሊዮኖች ያለቁባት፣ በአስር ሺዎች አካለ ስንኩላን የሆኑባት፡ በሚሊዮን የተፈናቀሉባት፣ ጥላቻ የነገሰባት፣ ሃይማኖቶች የተደፈሩባት፣ ድንበሯ የተጣሰባት፣ ሕገ ወጥነት የነገሰባት፣ ጉቦኝነት የተወደሰባት፣ ፍርሃት የነገሰባት አገር ለመሆኗ ያልተረዳ ካለ የአእምሮ ችግር የተጠናወተው መሆን አለበት። በተለይ ደግሞ አማራው በኢትዮጵያዊነቱ ከሚደርስበት ሰቆቃ በላይ  የዘር ማጥፋት ጦርነት ታውጆበታል። ባለፉት 5 ዓመታት መፈናቀል፣ በጅምላ ወደ እስር ቤት መወርወር፣ በየሄደበት መዋከብ፣ በዘመናዊ መሳሪያ በጅምላ መጨፍጨፍ፣ የሰብል መቃጠልና ንብረት መውደም፣ ባጠቃላይ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ያለማቋረጥ እየተካሄደበት ነው። ቀንደኛው የኦሮሙማ መሪ በከበባና በጦርነት፣ በረሃብና በበሽታ እንጨርሳቸዋለን ያለው እየተተገበረ እንደሆነ ግልፅ ነው። ዛሬ፣ እንኳን የእቅዱ ሰለባ የሆነው አማራው ቀርቶ መላው ዓለም በአማራው ላይ የዘር ማጥፋት ጦርነት እየተካሄደበት እንደሆን ተረድቶታል። የኦሮሙማው መንግሥት ሲኦል የሆነችን ኢትዮጵያ በመፍጠር የሚያጠፋውን ዘር አጥፍቶ የሚያሳምነውን አሳምኖ ኦሮሞ የምትመስል ኢትዮጵያ እፈጥራለሁ ብሎ አገሪቷን ማቅ አልብሷታል።

እራሱን የፌደራል መንግሥት ነኝ ብሎ የሚጠራው የኦሩሙማው መንግሥት የአንድ ነገድ መንግሥት ለማቋቋም ባለው እቅድ የትህነግን ወንጀለኛ ቡድን የእቅዱ አጋዥ አድርጎ በአማራ ላይ ባወጀው ጦርነት ትህነግን በድብቅ እያሳተፈ እንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ማንንታቸውን ባስከበሩ አካባቢዎች በተለይ በመከላከያ ስም የትህነግን ወታደሮች እያሰማራ ነው። እነዚህን የአማራ አፅመ እርስቶች አሳልፎ ለመስጠት ሬፈረንደም አካሂዳለሁ በማለት ልዩ ልዩ ደባዎችን በመጎንጎን ላይ ይገኛል። በእነዚህ አካባቢዎች አንዳንድ በአስተዳደሩ ውስጥም ሆነ ውጭ የተሰማሩ ተገዝተውም ሆነ ተታለው የዚህ ደባ ተባባሪ እንዳይሆኑ የትግሉ ኃይሎች በንቃት በመከታተል ላይ ናቸው።

በዚህ በአማራ ህልውና ላይ በታወጀው ዘርፈ ብዙ ጦርነት በግንባር ቀደምትነት የሚዋደቀው ፋኖ፣ የትግል አድማሱን ከቀን ወደቀን እያሰፋ፣ የኦሮሙማው መንግሥት አማራን ለማጥፋት የሚያካሂደውን ጦርነት ጀግንነት በተሞላበት፣ ዲስፕሊን በተላበሰና አለም አቀፋዊ የጦርነት ሕግጋትን በጠበቀ ሁኔታ ምላሽ እየሰጠ ነው። ፋኖ የጠራ ዓላማ ያለው ሕዝባዊ ጦር በመሆኑ ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቀውንና በመቶ ሺዎች የሚቆጠረውን ሞራለ-ቢስ የብልጽግና ሠራዊት መግቢያ መውጫ አሳጥቶ ሽንፈት በሽንፈት እያደረገው ነው።

ሕዝባችን መራር ትግል በሚያካሂድበት በዚህ ወቅት፣ በፌደራልና በክልሉ አመራር ደረጃ ላይ ሆነው አማራውን ለማስፈጀት የኦሮሙማው ብልጽግና ተላላኪ ሆነው እቅድ በማውጣትና በማስፈፀም በሕዝባችን ላይ የዘመቱ ይሁዳዎች አሉ። ለአነዚህ ከአማራ ቀንደኛ ጠላቶች ጋር ላበሩ ወገን-በላዎች ምንም ምክር የለንም። ምክር ህሊና ላለው ብቻ ስለሚሰራ አማራጩ መፋለም ነው። እንዲሁም በክልሉ ውስጥ በተለያዩ ደረጃዎች ያሉ ጥቂት ለሆዳቸው የተገዙ ወይንም የመንደር ስልጣናቸውን እንዳያጡ የሰጉና በዘረፋ የከበሩ ከሃዲዎች ሕዝባቸው የታወጀበትን ጥፋት በአይናቸው እየተመለከቱ ሚሊሺያ፣ ፖሊስና አድማ በታኝ በገንዘብ ገዝተው በማሰለፍ የኦሮሙማው መንግሥት አማራን በአማራ ማስወጋት ለሚለው እቅድ መሳሪያ ሆነዋል። ከዚህ ተግባራቸው ታቅበው ወደ ሕዝባቸው ካልተመለሱ መልሱ ሾህን በሾህ ይሆናል። ሌሎች ደግሞ አንድ እግራቸውን ብልጽግና ውስጥ ተክለው ሌላውን ሕዝቡ ውስጥ ከተው ቢቻላቸው ብልፅግናን ማዳን ካልሆነም የሕዝቡን አመፅ ለመቀላቀል አድብተው የሚሄዱ በተለይም በብልጽግና መካከለኛ እርከን ላይ ላሉ አንዳንድ ምሁራንና ሹሞች ምክር አለን።  ”ግመል ሰርቆ አጎንብሶ” እንዲሉ መስሏችሁ ነው እንጅ አማራው በአይነ ቁራኛ ይከታተላችኋል። በመፈረካከስ ላይ ካለው ብልፅግና ጋር ከመጥፋታችሁ በፊት አቋማችሁን እንድታስተካክሉ እንመክራለን።

ከአማራ ብልፅግና ጋር የተያያዛችሁ አንዳንድ ምሁራንና ከበርቴዎች ከብልፅግና የተለየ አደረጃጀት አለን ብላችሁ በማወናበድ የፋኖን ትግል ለማሽመድመድ የምታድርጉትንም ጥረት ከትዝብት ጋር ተገንዝበናል። ትህነግ ኢሕአደግ ሆኛለሁ ብሎ አወናብዶናል፣ ኦሮሙማ ብልፅግና ብሎ ጦርነት አውጆብናል። ስም አውጥታችሁ ተቀባብታችሁ ለሶስተኛ ጊዜ እናታላችኋለን ብላችሁ ለመምጣት እንዳታስቡ። ይህ ትግል ከትህነግ እስከ ኦሮሙማ ጠራርጎ የሚያጠፋ እና በብልፅግና መቃብር ላይ አዲሲቷን ኢትዮጵያ የሚገነባ ነው። ፋኖን የወታደራዊ አቅም ያለው ብቻ አድርጋችሁ ፋኖን የፖለቲካ ሥልጣን መወጣጫ ለማድረግ የጮሌ እቅድ ያወጣችሁ በውስጥም ይሁን በውጭ ያላችሁ ካላችሁ ተሳስታችኋል። ፋኖ ወታደራዊና የፖለቲካ ክንፎች አሉት። መሪ ድርጅትም ሆነ የጠራ አመራር የሚወጣው ከዚሁ ሕዝባዊ ትግል ነው። ስለሆነም፣

1/ በፌደራሉና በክልሉ የተጠለላችሁ ጥቂት አማራ ከሃዲዎች የአማራውን ትግል ለማሽመድመድ የምታካሂዱትን ፀረ አማራ ተግባሮች


እንድታቆሙ፤

2/ በገንዘብ ተገዝታችሁ የአማራውን የህልውና ትግል ለማኮላሸት ፋኖን እንድትወጉ ሰልጥናችሁ የተሰለፋችሁ የሚሊሺያ፣ ፖሊስና አድማ ብተና አባሎች ፋኖን በመቀላቀል ከሕዝባችሁ ጎን እንድትሰለፉ፤


3/ ይህ ትግል በብልፅግና ሽንፈት አይጠናቀቅም ብላችሁ በተፈረካከሰው ብልጽግና በማመን አንድ እግራችሁን ብልፅግና ውስጥ ያደረጋችሁ ምሁራን፣ የብልጽግና አባላትና ሌሎችም አድር ባዮች ሳይመሽባችሁ ወደ ሕዝባችሁ  እንድትመለሱ እንመክራለን።

ህልውናችንን በትግላችን እናረጋግጣለን!!

Featured Posts
Recent Posts
Search By Tags
No tags yet.
Follow Us
  • Facebook Classic
  • Twitter Classic
  • Google Classic

WELCOME

Welcome visitors to your site with a short, engaging introduction. Double click to edit and add your own text.

Start Now
david-whipple-mU-wz7JlJMc-unsplash_Ravid.jpg
bottom of page