top of page

Empower
Growth

ከጀመሩ መጨረስ ካረገዱ...

ጥቅምት 28 2013 ዓ. ም. (11/7/2020)


“ከጀመሩ መጨረስ ካረገዱ ማልቀስ”


ኢትዮጵያ ከትህነግ ማነቆ ትላቀቃለች

ወያኔ ከአፈጣጠሩ ገና ከጽንሱ ማንነቱ ግልጽ ነበር። አገር ለማፍረስ አውጠንጥኖና አቅዶ በኢትዮጵያ ላይ የመጣ መቅሰፍት ነው። የወጣለትም ፀረ-ኢትዮጵያ ድርጅት ነው። በ27 ዓመታት የግዛት ዘመኑ ውስጥ ያጠፋውን ጥፋትና በዚች አገር ላይ ያደረሰውን በደል ዘርዝረን የምንዘልቀውም አይደለም። ከሁሉም በላይ ግን በዜጎቻችን መካከል በቆየው ትልቁ እሴታችን በሆነው አብሮነት ላይ ያደረሰው ጉዳት በቀላሉ የምንወጣው አይደለም። ትህነግ የቀበረው ፈንጂ ገና ወደፊትም ጦሱ የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚፈትን ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔን ከስልጣን ኮረቻው ላይ አሽቀንጥሮ ከወረወረው በኋላ እንኳ ይህ ፈንጂ እየፈነዳ አያሌ ጉዳቶችን አድርሷል።

ሌላውን ትተን፣ ባለፉት ሶስት ዓመታት ህወሓትና ተባባሪዎቹ ያደረሷቸውን ጥፋቶች ብናነሳ፣ ጎንደር ውስጥ በታሪካችን ሆኖ በማያውቅ ሁኔታ በአንድነት ተጋምዶ/ተዛምዶ የኖረውን የቅማንትንና የአማራን ማሕበረሰቦች ለማጋጨት ባደረገው ጥረት ብዙ ዜጎች ሞተዋል፤ ተፈናቅለዋል፤ ንብረትም ወድሟል (በአሁኑ ወቅት ሁለቱ ማህበረሰቦች ሲያምሳቸው የኖረውን ወያኔን ለመፋለም በሕብረት ወደ ግንባር አምርተዋል)። በሱማሌ ክልል ውስጥ በጂጂጋና በአካባቢው ዜጎች ተገድለዋል፤ ተፈናቅለዋል። አብያተ ክርስቲያናት በሳት ጋይተዋል። ባለፈው ሰኔ ወር፣ በአርቲስት ሃጫሉ ሞት ሳቢያ፣ በኦሮምያ ግዛት ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች በወያኔ አስተባባሪነት፣ በኦነግ ሸኔ ፈጻሚነትና በኦሮሚያ መንግሥታዊ መዋቅር ውስጥ በተሰገሰጉ የመንግሥት አባሎች አስተናጋጅነት ብዙ ዜጎቻችን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፣ ተሰደዋል፣ ንብረታቸውም ወድሟል። በቤኒ ሻንጉል በተደጋጋሚ በተለይ በአማራ ላይ ያተኮረ ግድያዎች ተካሂደዋል፣ ብዙ ንብረት ወድሟል፤ ዜጎች ተሰደዋል። አሁንም ሃይማኖትንና ቋንቋን ማእከል ያደረገ ሕዝብን ከሕዝብ የማጋጨት ተግባር በስፊው ሲካሄድ እያየን ነው።

ባለፈው ሳምንት የሩዋንዳን አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ታሪክ በሚያስታውስ ሁኔታ ምዕራብ ወለጋ ውስጥ ጉሊሶ በተባለው ቦታ አማራዎችን ለስብሰባ ጠርተው ህፃን፣ ሽማግሌ፣ ሴት፣ ደካማ፣ እርጉዝ ሳይሉ በመትረስ አጭደዋቸዋል። በቦምብ አጋይተዋቸዋል። ይህ የሆነው ደግሞ መከላከያ ከቦታው ለቆ እንደወጣ በመሆኑ የአካባቢው የመንግሥት መዋቅር ትብብር እንዳለበት አያጠራጥርም። ወያኔ ለፕሮፖጋንዳ ፍጆት ብሎ የራሱን ሕዝብ ተንቤን ገብያ ውስጥ በቦምብ ያስደበደበ ነው። መሬት ለመቀማት በወልቃይት ጠገዴ የዘረ ማጥፋት ወንጀል የፈጸመ ድርጅት ነው። ሰይጣን እራሱ ሰይጣንነትን ከወያኔ ቢማር አይደንቀንም። ይህ ሁሉ ፀረ-ኢትዮጵያ ሁከት በህወሓትና በኦነግ ሸኔ የሚካሄድ ለመሆኑ ለማንም የተሰወረ አይደለም። መግለጫ ማውጣትና በቃል ወጥቶ ማውገዝ ወይንም ሙሾ ማውረድ በቂ አይደለም። መንግሥት ከሕዝብ ጋር ተባብሮ በእነዚህ ድርጅቶች ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰድ ብቸኛው አማራጭ ነው።

በዚህ አጋጣሚ ለተገደሉ ወገኖቻችን ሃዘናችንን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው መጽናናትን ይስጥልን እንላለን። ለታሰሩ፣ ለተሳደዱ፣ አካላቸው ለጎደለና ንብረታቸው ለወደመባቸው ዜጎች በመንግሥት አስፈላጊው ካሳና ድጋፍ እንዲደረግላቸው እናሳስባለን። አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲያቀርብም እንጠይቃለን።

ይህ አጥፊ ድርጅት ይህ ሁሉ ጥፋት አልበቃውም። እብሪተኛውና ካሃዲው ወያኔ ኢትዮጵያን ቀውስ ውስጥ ጨምሮ ለመበተን ያለመውን ቅዠት እውን አደርጋለሁ ብሎ ባለፈው ማክሰኞ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊታችን ላይ በትግራይና በጎንደር ጥቃት ፈጽሟል፤ ጉዳት አድርሷል፤ መሳሪያም ለመዝረፍ ሞክሯል። በተለይም ዳንሻ ላይ ብዙ ጉዳት ያደረሰ ቢሆንም መከላከያ ሠራዊቱ በክልሉ የጸጥታ ኃይልና በሚሊሺያው እየተረዳ የወያኔን እቅድ ማክሸፍ ችሏል። በጠገዴ ቅራቅር ላይ ጦርነት ከፍቶ አይሸነፉ ሽንፈት ደርሶበታል። ወገኖቻቸው በሞት ያለቁባቸው፣ በሰቆቃዊ እስር ቤቶች የሚማቅቁባቸው፣ ከቀያቸው የተፈናቀሉባቸው የወልቃይት፣ የጠገዴ፣ የጠለምት፣ የራያ ወገኖቻችንና መላው የአካባቢው ሕዝብ ከመከላከያ ሠራዊታችንና ከአማራ ልዩ ኃይል ጎን ተሰልፈው እየተዋደቁ ነው። አስፈላጊውን እርዳታ ሁሉ እየሰጡ ናቸው። ለሰላሳና ለአርባ ዓመት የከፈሉት መስዋእትነት አሁንም ቀጥሏል። ዛሬ ባስለቀቋቸው አካባቢዎች የነፃነት አየር እየተነፈሱ ነው። የወያኔ የጭቆና መረብም በመበጣጠስ ላይ ነው። እስካሁን ማንነቱን የተነፈገው ሕዝብ ባገኘው አዲስ ነፃነት የወያኔን የጭቆና አስተዳደር ቀንበር አሽቀንጥሮ ጥሎ የእራሱን አስተዳደር በመመስረት ላይ ይገኛል። ማንነቱን ከማስመለስም ወደ ኋላ አይልም።

ትሕነግ ከውጭ ጠላት ወግኖ ኢትዮጵያን ለመውጋት ወደ ኋላ የማይል ድርጅት ነው። ሁልጊዜ የምንለውን ዛሬም እንደግመዋለን። ላለፉት 30 ዓመታት ኢትዮጵያን በጽኑ ያደማው ወያኔ ከነሸንኮፉ ተነቅሎ ካልወደቀ፣ ኢትዮጵያ እረፍት አታገኝም። በኢትዮጵያዊነት የሚያምን ሁሉ የወያኔን መኖር ሊቀበል አይችልም። ይህ ጦርነት በኢትዮጵያና በፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች መካከል የሚደረግ ጦርነት ነው። የፌደራሉ መንግሥት በወያኔ ላይ የማያዳግም እርምጃ የመውሰድ ግዴታ አለበት።

የጎንደር ሕዝብ፣ መላው የአማራ ሕዝብና ኢትዮጵያውያን ሁሉ በመዋደቅ ላይ ላለው መከላከያ ሠራዊታችን፣ የአማራ ልዩ ኃይላችንና ሚሊሺያችን ድጋፍ መስጠትና በማንኛውም ረገድ ተሰልፎ መርዳት የዜግነት ግዴታችን ነው።

ህወሓት ኦነግ ሸኔና ግብረ አበሮቻቸው በኢትዮጵያ ላይ የሰነዘሩት ጥቃት በማያዳግም ሁኔታ ይመታል።

የወልቃይት፣ የጠገዴ፣ የጠለምትና የራያ ሕዝብ ማንነቱን ያስመልሳል!

ሞት ለህወሓትና ኦነግ ሸኔ!

ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!Featured Posts
Recent Posts
Search By Tags
No tags yet.
Follow Us
  • Facebook Classic
  • Twitter Classic
  • Google Classic

WELCOME

Welcome visitors to your site with a short, engaging introduction. Double click to edit and add your own text.

Start Now
david-whipple-mU-wz7JlJMc-unsplash_Ravid.jpg
bottom of page