top of page

ጀግናው ኮሎኔል እምሩ አረፉ

www.gonderhibret.org 4126 Deerwood Trail, Eagan MN 55122 Tel 651 808 3300 ሰኔ 21፣ 2013
ዛሬ እዚህ ተገኝተን የምንዘክረው ታላቅና የኢትዮጵያ ብርቅዬ ሰው የሆኑትን ኮሎኔል እምሩ ወንዴን ነው። ገና ከልጅነት ዕድሜአቸው ጀምሮ የተጣሉባቸውን የተለያዩ ከባድ ሀላፊነቶች በብቃት የተወጡ አገር ወዳድ ጀግና ነበሩ። የተባበሩት መንግሥታት ባካሄደው የኮርያ ዘመቻ የቃኘው ሻለቃና የኢትዮጵያን ሥም ካስጠሩና ዕውቅና ካስገኙ ጀግኖች መካከል አንዱ ናቸው።
ኮሎኔል እምሩ አገራቸውንና ወገናቸውን በጣም የሚወዱና በአገራችን የዴሞክራሲ ለውጥ እንዲመጣ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለዋል። በዚህም ምክንያት በተለያዩ መንግሥታት ለእሥር ተዳርገዋል። ቤተሰባቸውንና የሞቀ ኑሯቸውን ትተው በረሀ ወርደው ለህዝብ መብትና ነፃነት ለአያሌ ዓመታት በአገራቸው ምድርና በውጭ አገር እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ሲታገሉ ኖረዋል። የጎንደር ክፍለ-ሀገር አስተዳዳሪ በነበሩበት ጊዜ የአያሌ ወጣቶችን ህይወት ከቀይ ሽብር መቅሰፍት የታደጉ በክፉ ቀን ለወገናቸው የቆሙ መሰል የማይገኝላቸው ሰው ናቸው።
ኮሎኔል እምሩ ወንዴ ለአገራቸውና ለወገናቸው ያበረከቱት አገልግሎትና አስተዋፆ ታሪክ ሲዘክረው ይኖራል። የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት አባላት በሙሉ እኒህ አገር-ወዳድ ጀግና ለአገራቸውና ለወገናቸው ለከፈሉት መሥዋዕትነትና ላበረከቱት አስተዋፆ ሁሉ ያለውን ከፍተኛ አክብሮትና በዕልፈታቸው የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ለቤተሰቦቻቸው፤ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለሚያውቃቸው ሁሉ ይገልፃል። ሀያሉ ልዑል እግዚአብሄር ነፍሳቸውን በዓፀደ ገነት ያኑርልን! ለቤተሰቦቻቸውም መፅናናቱን ይስጥልን።
ጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት

Featured Posts
Recent Posts
Search By Tags
No tags yet.
Follow Us
  • Facebook Classic
  • Twitter Classic
  • Google Classic
bottom of page