የጎንደር ኩራቱ፤ ክብሩ ነጻነቱ
ጎንደር ኩራቱ፤ ክብሩ እና ነፃነቱ፤
ዛሬ ይህን እርዕሥ የመረጥነው ያለ ምክንያት አይደለም። ግን በዕውነት ላይ በመጀመራችን ጸናችሁ እንጂ ጠበባችሁ አትበሉን፤ ጠባብ ብሄርተኝነትን ወይም ግንጠላን አላቀነቅንም እና። ለዚህ ርዕሥ ምክንያታችን፤ ጎንደር፤ ኢትዮጵያን ለመውረር እና የአባይን ውኋ እንደልባቸው ሁል ጊዜ ለመጠቀም ከሚሹት አገሮች አንዷ ከሆነችው ሱዳን ጋር ይዋሰናል። በዚህም ምክንያት በየጊዜው ያለማቋረጥ ድንበራችን ጥሰው ለመግባት የሚያደርጉትን ሙከራዎች ለመመከት ግንባር ቀድም መሥዋዕትነት የሚከፍለው፤ የጎንደር ሕዝብ ነው። አፄ ቴውድሮስ ተሽፍትነት እስከ ንግሥና ድረስ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለማስከበር ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ሲንቀሳቅውሱ አብሮ በመዝመትና በሱዳን በኩል ያለውን ጠረፍ በማስከበር ከፍተኛውን ድርሻ ያበረከተው ጎንደሬ ነው። አጼ ዮሐንስ ከድረቡሺ ጋር ሲዋጉ ከመጀመሪያው እስከ ድሉ ድረስ የጦርነት ገፈቱን የቀመስው የጎንደር ሕዝብ ነው። በአሁኑ ጊዜ ደግሞ፤ የወያኔ መንግሥት ዳር ድንበራችን ለሱዳን ቆርሶ ለመስጠት የሚያደርገውን ድረድር እየተቃወመ፤ ድንበር ዘለል የሱዳንን ገበሬዎችን እያባረረ፤ አንድ ጋትም ቢሆን “መሬታችን አሳልፈን አንሰጥም” በማለት፤ ለአገር ነፃነት እራሱን አሳልፎ እየሰጠ ያለው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አካል የሆነው ጎንደሬው ነው። አሁን በቅርቡ ገበሬዎቸና ወታደሮቸ ተጨፈጨፉ እያለ የሱዳን መንግሥት የሚያቅራራው፤ ድንበራችን ዘለው በወታደረ ታጅበው መሬታችን ለማረስ የመጡትን ጠራርጎ ወደ መጡበት ስለመለሳቸው ነው።
ይህን አገር ወዳደነቱን የሱዳን መንግሥትም ጥሩ አድረጎ ስለሚያውቅ ነው፤ ወያኔ ሥልጣን እንደያዘ የድሮው ጠቅላይ ሚኒስተር ታምራት ላይኔና የሱዳኑ የአክራሪ እስልምና መሪው ቱራቢ በጋራ ካርቱም ላይ ባደረጉት ውይይት አማራውን ለመምታት ጎንደርን መምታት ነው የሚል ስምምነት ላይ የደረሱት። ለዚህም ነው እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ ወያኔ የጎንደር አገር ወዳዶችን እና ምሁራንን እያፈነ መዳረሻቸውን የሚያጠፋው። ስለሆነም ነው ከላይ የተጠቀሰውን አርዕስት የመረጥነው። ከዚህ በላይ ያለው የመኖር ትርጉም ደግሞ በታሪክ እና በተጨባጭ እንደምናዬው፤ ከክፍለ ሀገር ባሻገር፤ ከአገር አቀፍ ነፃነቱም ጋር እጅግ ተያያዥ መሆኑን ነው። የመሳፍንቱ ከፋፍለህ ግዛው፤ አልዋጥ ያለው ጎንደሬ፤ አፄውን ከማህከሉ በመምረጥ እስከ መቅደላ ድረስ ዘልቆ፤ “ኩራቴ ነፃነቴ” በሚል ለአንድነቱ እና ለኢትዮጵያዊነቱ በኩራት እና በቆራጥነት ከፍተኛ መሥዋዕትነት ከፍሏል። ከድርቡሾች እና ከግብፆች ጋር አንገት ላንገት ተናንቋል። የዛሬ ኢትዮጵያዊነታችንን ክብር ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አጎናጽፏል። እስከ አሁኗ ደቂቃም ድረስ፤ በተለያዩ ጊዚያቶች፤ ድምበራችን አልፈው፤ መሬታችን ለመውሰድ ጊዜን እና ሁኔታን እየተጠቀሙ ለሚስገበገቡ የሱዳን መሬት ጥመኞች፤ ምሳቸውን እያቀመሰ ኖሯል፤ አሁንም ያን ታሪኩን እየደገመ ይገኛል።
ይህ ብቻ አይደለም፤ በአገራችን ያለፉ መንግሥታት መጠን ያለፈው የአሥተዳደር ግፍ ጽዋቸው የሚፈሰው ወይም ተዘቅዝቆ የሚደፋውም በቆራጡ ጎንደሬ ጀግንነት ቆራጥ ትግል እንደሆነ የሚያውቁት ሃቅ ነው። ይህንም ደግሞ ያሁኑ ወያኔ ሳይቀር፤ በነማን የጎንደር ጅግኖች ሐይል ምኒሊክ ቤተመንግሥት መግባት እንደቻለ ጠንቅቆ የጎንደር ሕብረት 2 ያውቀዋል። የቤተ መንግሥት አሰናባቹም እንዲሁ ጎንደሬው እንደሆነ በሚገባ ያውቀዋል። ለዚያም ነው፤ ከመጀመሪያው ጀምሮ ጎንደርን መከፋፈል እና ታሪካዊ መልክዓ ምድሯን እንዳልነበረ ለማድረግ አልሞ እና አቅዶ የተነሳው። እቅዱን የጀመረው ገና ትግራይ መሬትን ሳይለቅ፤ ወልቃይት ጠገዴን እና ጠለምትን የትግራይ ክልል አድርጎ በወደፊት ካርታው ላይ በማስቀመጥ ነው። በጎንደር ክ/ሀገር እንዴት የጎሳ ችግርን መጫር እንዳለበት አልሞ እና እንዴት የጎንደርን መሬት ማሳነሥ እና ለጎንደር ታሪክ ባለቤትነት የሚሰማቸውን የቅማንት እና የአማራ ጎሳዎች ማቃቃር እንዳለበት እና ሁለቱ በጠላትነት ሲተያዩ እና ሲናቆሩ፤ በካርታው ሊያጠቃልል ያሰበውን የጎንደር መሬት ካጠናቀቀ በኋላ እንዴት በሰላም መኖር እንደሚችል ተንኮሉን አርቅቋል። ይህን መሰሪነቱን የተረዱ በውጭም አገር ቤትም ያሉ ብልህ እና አርቆ አሳቢ የቅማንት ብሔረሰብ ተወላጆች፤ በጎንደር ታሪክ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸውን፤ ለረዥም ዘመናት አብረው፤ በጋብቻ፤ በቋንቋ እና በሐይማኖት ተዋህደው አገራቸውን ከጠላት፤ ኑሯቸውን ከችግር ተከላክለው፤ ሁለንተናቸውን አዋህደው የኖሩ በሁለትነት እንደ አንድ የሚቆጠሩ ጎሳዎችን መለያየት የማይቻል መሆኑን ከወዲሁ አሥመስክረዋል።
ይህ የመክፋፈል ተግባራቸው ያልተሳካላቸው፤ የወያኔ ካድሬዎች ግን አሁንም ይህን ህብረተሰብ በቁጣ ለማነሳሳት የሚፈነቅሉት ድንጋይ አላጡም። ሰበብ ፈጥረው በገበያ ላይ የንጹሃንን ደም አፍሥሰዋል። በሰላም ያለወሰን በማንኛውም ቦታ አርሰው ይኖሩ የነበሩ የቋራ እና የታች ጭልጋ አካባቢ አርሶ አደሮችን ከማሳቸው እንዲፈናቀሉ አድርገዋል። አሻፈረኝ ለማለት የሞከሩትንም አፍነው ዘመድ በማይጠይቃቸው እስር ቤት አጉረዋል። ይህ እንደሚመጣ ግን፤ ቀድመው የወያኔን የጎሳ ነፃነት ተብዬ ፖለቲካ ኪሳራ የተረዱ በውጭ የሚኖሩ የቅማንት ተወላጆች በ”ይድረስ የጎንደር ሕዝብ” ቁጥር አንድ እስከ ሦስት ባወጡት፤ እና ጎንደር ሕብረት ከተመሰረተም በኋላ እስከ ቁ.6 የቀጠለው መግለጫችን አተኩሮ፤ አንቀጽ 39ኝን መሰረት አድርጎ የሚነሳ የጥቂቶች አስመሳይ ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ፤ በመላ አገራችን በተግባር እንዳየነው ውጤቱ ወይም ምላሹ የከፋ፤ ከኮሶም በላይ የመረረ እንደሚሆን ያሳሰብነው። ይህ መሆኑ እየታወቀ ግን፤ ለተለያዬ የፖአለቲካ ፍጆታቸው ሲሉ ጠባብ ጎሳኝነት ለሚራምዱ መሪዎች፤ ለሚጠፋው ህይወት በታሪክ እንደሚያስጠይቃቸው አስጠንቅቀን ነበር። አሁንም እጅግ አስጠያቂ ነው!! የጎሳ ነፃነት ብሎ ማሰብ፤ መዘዙ ከአካባቢው ቀርቶ ከጎረቤት ጋር በሰላም የማያኖር የኑሮ መርዝ እንጂ፤ የነፃነት ጠብታ የለውም። ነፃነት ከግለሰብ ሰብአዊነት የሚጀመር እንጅ፤ እድላቸው በእረኛች እንደሚወሰን የከብቶች መንጋ ነፃነት፤ በጎሳ ዋጋ ከፋዩ የወያኔ እጅ የሚታፈስ የሃያ አምሥት ዓመት እውነታ ሆኖ አላገኘነውምና። እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለብሔራዊ አንድነቱ እና ለግለሰባዊ መብቱ በጋራ ለመታገል ሕብረት እየፈጠረ ባለበት ወቅት ላይ፤ ጊዜው ባለፈበት የጎሳ ማነቆ ውስጥ መፈራገጥ፤ የማንንም ኢትዮጵያዊ ትኩረት የማይስብ አጉል መስዋዕትነት እና የህብረተሰባዊ ቀውስ ኪሳራ መፈጸሙ ነው። ከላይ ያሥቀመጥናቸው አዲስ ክስተቶች ቢመሥሉም፤ የተወልዱት ግን፤ ከተናንት የወልቃይት ጠገዴ ወገኖቻችንን ግፍ እና በደል ማህፀን ነው።
የወያኔ አገር በቀል ጠላቶች፤ አይናችን እያየ፤ በጠራራ ፀሐይ፤ ታሪክ አዋቂ፤ የሆኑትን የአካባቢ ተወላጅ አባዎራዎችን እያፈኑ ድዝባቸውን ሲያጠፉ እና ለም መሬታችን ወደ ትግራይ ሲከልሉ፤ ሁሉንም በዬተራ የሚያደቀው የወያኔ ግፍ በያንዳንዳችን ቤት ዘልቆ እስኪገባ ድረስ በዝምታ በመመልከታችን፤ ጎንደሬ ለክብሩ እና ለነፃነቱ ዋጋ መሥጠቱን የረሳ ሥለመሰለው፤ የከፋፋይ አጀንዳውን፤ በማባዛት ዛሬም፤ ጎንደርን የጎንደር ሕብረት 3 በቅማንት እና በአማራ ሊሰነጥቃት ተነሳ። ሆኖም ግን፤ ይህ ዘመን ያለፈበት የሥልጣን እድሜ ማራዘሚያ ከፋፋይ ደባ እንደማይሳካ የምናየው ሐቅ፤ ከሃያ አምሥት ዓመት በኋላ፤ በደሙ እና በአጥንቱ ጎንደሬነቱ የታነጸው ተተኪው አዲሱ የወልቃይት ተወላጅ፤ “እኛ ጎንደሬም አማራም ነን እንጂ፤ ትግሬ ሆንነ አናውቅም” በማለት ከዳር እሥከ ዳር ያቀጣጠሉት ሰላማዊ ትግል፤ ከላፈው ስህተት በመማር፤ የሁሉም ጎንደሬ ትግል ሆኖ ዳር እስከ ዳር መታገዝ ይኖርበታል። ዬንሰሳዊነት ባህሪ ያለውን፤ ከሌላው ወገኑ ጋር በሰላም አብሮ በማያኖር የጎሳ አጥር መሥፈርቱ ያላደረገን ለማንነቱ የሚታገልን አንድ የህ/ሰብ አካልን መደገፍ እና የኔ ብሎ ማገዝ ደግሞ ዬዕውነተኛ ኢትዮጵያዊንትና የዲሞክራሲያዊ ትግል አንዱ አካል በመሆኑ በውጭው ዓለምም ይሁን ውስጥ ያለን ኢትዮጵያውያን በሚቻለን አቅም ሁሉ ማገዝ ያለብን ወሳኝ ወቅት ላይ መሆናችን ለማስገንዘብ እንወዳለን። እንዲህ አይነቱን ትግል ለማክሽፍ፤ መሰሪው የወያኔ ሥራዓት፤ ቢችል በጎሳ ካልቻለ ደግሞ በወረዳ እና በአውራጃ ለመክፋፈል ከራሳችን አብራክ የወጡ ሆድ አደር ካድሬዎቹን አሥርጎ በማሥገባት፤ ሊከፋፍለን ሁሌ እንደሚጥር አይተናል። እናም ሕዝባችን፤ ለአንዴ እና ለመጨረሻ እኒህን ከአብራካችን ወጥተው በሆዳቸው እየሸጡን ያሉ ዘመናዊ የወያኔ ካድሬዎች፤ ከዚህ በኋላ ሊመከሩ እና ከጎናችን ሊቆሙ፤ ካልሆነ ሊመነጠሩ ይገባል። የዛሬ ዘመነኞች፤ የነገ ለማኞች እንደሚሆኑ ደግሞ፤ የደርግ ግፈኛ ካድሬዎች እጣ ምን እንደሆነ ዞር ብሎ የትናንቱን ታሪክ ማሥታወስ የወቅቱ ግዴታቸው ነው እንላለን።
ሌላው፤ ክ/ሀገራችን ጎንደር፤ በአገር በቀል የወላድ ጡት ነካሽ ልጆቿ ከመታመሷ በላይ፤ ተቆርቋሪ መሪ አለመኖሩን የተረዱት የሱዳን መሬት ጥመኞች፤ ወሰናችን አቋርጠው ወደ መሬታችን ዘልቀው በመግባት ወግኖቻችን አፍነው በመውሰድ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ አንገታቸውን እያረዱ በመጣላቸው፤ ለዘመናት ራሱን እና ድንበሩ አስከብሮ የኖረት አኩሪው የአርማጭሆ፤ የጭልጋ እና የቋራ ወገኖቻችን እየፈጸሙት ያለውን ጀግንነት፤ የመላው ጎንደርም ሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ ትኩረት እንዲሰጠው እና በሞራል እና በቁሳቁስ እንዲሁም በመገናኛ ብዙሃን ሽፋን በመሥጠት ለመላው ዓለም ሁኔታዎችን በማጋለጥ እንድንተባበር እና ለብሔራዊ አንድነታችን ብሎም ዲሞክራሲያዊ ነፃነታችን በጋራ እንድንቅቆም እናሳስባለን። በተጨማሪም፤ ድንበርክን ለማሥከበርም ይሁን ለዲሞክራሲያዊ ትግሉ ያግዝ ዘንድ አቅምህ እና እድሜህ በፈቀደው መጠን ሁሉ፤ ማንኛውም የጎንደር ሕዝብ ራስክን በማሥታጠቅ፤ “ጀግና መሪውን ይወልዳል” እንዲሉ የአካባቢህን ቆራጥ ጀግኖች ከፊትህ በማውጣት እና መሪ በማድረግ በጎንደር ሕብረት ጥላ ሥር ተደራጅትህ በማንኛውም ሥራዓት ውሥጥ በፌደራል ደረጃ ጎንደርን ወክሎ ጥቅምህን የሚያስከብር ድርጅት እንዲኖርህ ከአሁኑ ታገል።
ከዚህ በላይ በዘረዘርናቸው እና በመሳስሉት ግፍ እና በደሎች ምክንያት በመነሳት፤ ከአብራክህ የወጡ ልጆችህ የጎንደር ሕብረትን ከመሰረቱ በአንድ ዓመት ውስጥ፤ በሰሜን አሜሪካ እና በአውሮፓ እንዲሁም በሆሻእና እና በአውስታራሊያ በሥፋት ተደራጅተው በመንቀሳቀሥ ላይ ይገኛሉ። በተለይም፤ ባለፈው መሥከረም ፲፱/፳፻፰ ዓ. ም በዋሽንግተን ዲሲ የጎንደር ሕብረት ቀጠና በተደረገ ዝግጅት፤ የተለያዩ አይነት ሙያ ያላቸው ሙሁራን እና ተቆርቋሪ ጎንደሬ/ኢትዮጵያውያን የተሳተፊበት፤ በሦስት ፕሮፈሰሮች ጥናታዊ ጽሁፍ አቅራቢነት፤ ከወልቃይት አካባቢ ተወላጆች ልሳነ ግፉአን በተጠናከረ ዘገባ ዝግጅት፤ በጎንደር ሕብረት መሥራች አመራሮች ድርጅታዊ ሂደት እና የጎንደር ሕብረት 4 ጥናካሬ ዘገባ አቅራቢነት፤ በተካሄደው የአንድ ቀን ጉባኤ፤ የታየው ተሳትፎ እና ለወደፊት የቀደደው ብሩህ የጎንደር ሕብረት ተሥፋ እጅግ አበራታች እና ወኔ ቀሥቃሽ ነበር ማለት ቢያንሰው እንጂ ማጋነንን አሆንብንም። በመሆኑም፤ መላው የጎንደር ሕዝብ ይህን መንፈስ ሊወርሰውና በየአካባቢው ሊያስፋፋው፤ ሊያሳድገው ይገባል እንላለን። ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ፤ የጎንደር ሕብረት።