የትግራይ ሰዎች ተፈናቀሉ: አጉል የወያኔ ጩኸት በሽንፋ-ጎንደርAbebe GelagayJun 28, 20161 min readላለፉት 40 ዓመታት አገርን በማፈራረስ አባዜ የተጠመደው ወያኔ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር ሲፈልግ የትግራይ ሕዝብ ልጆቹን ስለሰዋ የትግራይ ግዛት መስፋት አለበት፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ አባላቶቹን አደራጅቶ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በማስፈር፣ ብሎም ከባንክ ብድር በገፍ እንዲያገኙ በማድረግ በሰፈሩባችቸው አካባቢዎች ሁሉ የንግድና የእርሻ ሥራዎችን በበላይነት እንዲይዙ አድርጓል። ስለሆነም ወያኔዎች ተደራጂተው በሰፈሩባችው አካባቢዎች ሁሉ የአካባቢው ተወላጅ በራሱ ቀዬ የበይ ተመልካች እንዲሆን ተደርጓል ። በአጭሩ ወያኔዎች ለ25 ዓመታት በመላ ሀገሪቱ የሚያካሂዱት ዘረፋና የማያባራ የግዛት ተስፋፊነት ሌላው ቀርቶ በራሳቸው አምሳል የፈጠሯቸው አጫፋሪ የጎሣ ድርጅቶች እንኳ ገደብ የለሹን የወያኔ ሁሉም የኔ ይሁን በሽታ ሥራ ላይ ለመትግበር ከአቅማቸው በላይ እየሆነ መጥቷል።
Comments