በሰላማዊ ሕዝብ ላይ የሚደረገው ጭፍጨፋ በአስቸኳይ ይቁም!!!Abebe GelagayJul 13, 20161 min readበሰላም ሥርቶ በሚበላው የጎንደር ከተማ ሕዝብ ላይ የወያኔ/ኢህአዴግ መንግሥት ልዩ የአፋኝ ጦር አሰማርቶ በሰው ህይዎትና በንብረት ላይ ከፍተኛ የሆነ ጎዳት ማድረሱን ከተለያዩ የዜና አውታሮች እና የከተማው ኗሪ ከሆኑ የጎንደረ ተወላጆች ለማረጋገጥ ችለናል። ጭፍጨፋው አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን እነዚህ የአይን እማኞች አረጋግጠዋል። በደም የጨቀየው የወያኔ መንግሥት ያለደም መዋል ማደረ የተሳነው ይመስላል።
Comments