የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ! ነፃነትህ በደጅህ ቆማለችና እነሆ ግቢ በላት ! ከልሳነ ግፉዓን ድርጅት የተሰጠ መግለጫ
ጎንደር ስለፍቅር ሞትን ይታገሳል! ስለሰላም እልፍ ይጓዛል! የጎንደር ህዝብ ለአለፉት 25 ዓመታት በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ወገኖቻችን ላይ ያደረሰውን የዘር ማጽዳት ወንጀልና የጎንደር ታሪካዊና ለም መሬቶችን ወደ ትግራይ በመከለል በትግራይ ሰፋሪዎች የማጥለቅለቁን የእብሪትና የግፍ ጉዞ በሰላማዊ መንገድ እንዲቀለበስና ችግሩንም በህግ አግባብ ብቻ ለመፍታት ሲል ብቻ ትግስት አስጨራሹንና የተንዛዛውን የህወሃት የህግ ተቋማት ሂደት በትእግስት በመከታተል እስከ መጨረሻው ሰአት ድረስ ለሰላምና ለፍቅር ያለውን የሚደነቅ ፅኑ አቋም አሳይቷል።