Search
የጎንደርን ታሪካዊ ሰልፍ አስቦ ስለመዋልና ለኢትዮጵያን የነጻነት ትግል ድጋፍ ስለመስጠት
- Abebe Gelagay
- Jul 4, 2017
- 1 min read

የጎንደር ህዝብ ባለፈዉ ዓመት (ወርሃ ሃምሌ 5 ቀን 2008 ዓ/ም) ወያኔ ያጠመደዉን መትረየስ ተረማምዶ የ25 ዓመታታት የግፍ የዘረኛ ሥርዓት ለመገርሰስ በጎንደር ከተማ የአምባሻ ባንዲራ አሽቀንጥሮ ጥሎ ለዘመናት የነፃነቱ ምሳሌ የሆነችውን ሰንደቅ አላማዉን እያዉለበለ፤ “የኦሮ ደም ደማችን ነው፤ ቅማንት እና አማራ አንድ ነው፤ አንክፋፈልም” በማለት የፍርሃት ኬላን ሰብሮ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሔራዊ መልክቱን ማስተላለፉ ይታወቃል። በሚሊዮን የተቆጠረ ሰልፈኛ ጎዳናዎችን አጨናንቆ የጎንደር ሕዝብ በዚያች ቀን ያስተላለፈዉ የትግል ጥሪ ወያኔን በእጅጉ ያብረከረከ የኦሮሞና አማራን ወንድማማችነት ያስመሰከረ፤ የትግል ማዕል ሁኖ ዓለምን ያስደመመ፤ አስደናቂ እና የማይረሳ ታሪካዊ ቀን ነዉ።
Comentários