ጎንደር ዛሬም ታሪክ ሰራAbebe GelagaySep 26, 20171 min readወያኔ ከደደቢት በርሃ ይዞ የመጣውን የትግራይ ተስፋፊነት ተግባራዊ ለማድረግ ሲል ጎንደር ላይ ቅማንትና ዐምሐራን በመለያየት እሳት አንድዶ፤የመሬት ተሥፋፊነቱን ተግባራዊ አድርጎ ትግራይ ላይ ቁጭ ብሎ በመንፈላሰስ እድሜውን ለማራዘም ያቀደውን፤ሕልም የጎንደር ሕዝብ አከሸፈው። ጎንደሬው ቅማንትም ዐምሐራም አንድ ነን በማለት በምክር አልሰማ ያሉትን፤በሰፌው የልዩነት ፕሮፓጋንዳ ሲያላዝኑ የከረሙትን ቀንደኛ የወያኔ ካድሬዎችን በምርጫ ካርዱ የሃፍረት ሸማ አካናንቦ አንድነቱን አረጋግጦ “አርፋችሁ ተቀመጡ” ብሎ ወደ መጡበት መልሷቸዋል። ይህን ብዙ የተደከመለትን የከፋፍለህ ግዛው የጎሳ ፖለቲካ በጎንደር ሕዝብ አፈር ድሜ ሲገባ ማየት፤ ለጎንደሬዎች፤ የአንድነትና የጀግንነት ታሪክ ምሥክር መሆኑን በማረጋገጣችን፤ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የአንድነት ተስፋና ኩራት ነው ብንል አናፍርበትም።
Comments