ጅምሩ ይሳካ ዘንድ ሁላችንም እንደመር!የጎንደር ሕብረት (ጎሕ)Jun 29, 20181 min readኢትዮጵያ አገራችን ስንል ወደኋላ በህሊናችን ተጉዘን፤ ጠልቀን ታሪክን ዘክረን ስንመረምራት በእሳት እንደተፈለቀቀ ወርቅ የአኩሪም የአስከፊም ቅንብሮች መልካም ውጤታችን ናት። ጀግኖች አባቶቻችን አገር ሲወረር፤ ክብር ሲደፈር በአንድነትና በህብረት፤ በቆራጥነትና በጀግንነት አብረው በመቆም በአጭር ጊዜ ውስጥ ውቃይኖስ አቋርጠው፤ ድምበር ጥሰው ዘልቀው በመግባት የደፈሩንን የውጭ ጠላቶቻችን በማሳፈር የተጣሰ ድንበራቸውን፤ የተደፈረ ክብራቸውን አስከብረው ዘመንን ተሻግረው ለደረስንበት አኩሪ ታሪክ ባለቤት እንድንሆን የህይወት ዋጋን ከፍለውልናል።
Commentaires