ሰላምና ልማት የሚገኘው የመኖር ህልውና ሲከበር ነው !
ሰላምና ልማት የሚገኘው የመኖር ህልውና ሲከበር ነው ! ወቅታዊ መግለጫ የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ከተመሰረተ ጀምሮ ላለፉት አራት አመታት የትግራይ ነፃ አዉጭ ግንባር በአማራዉ ህዝብ ላይ በተለይም በጎንደር ሕዝብ ያነጣጠረዉን መጠነ ሰፊ ግፍና ሰቆቃን በመቃወም ህዝባችን የተጋፈጠዉን የነጻነት ተጋድሎ በመርዳት የድርሻዉን ሲያበረክት ቆይቷል። ወደ ትግራይ በግፍ የተወሰዱትን የሁመራ፥ ወልቃይት፥ ጠገዴ እና የጠለምት ወረዳዎች ወደነበሩበት ጎንደር ክፍለ ሃገር እንዲመለሱ፤ የአማራና ቅማንትን ማህበረሰብ ለመከፋፈል በሴራ የተወጠነዉን የጥፋት ዘመቻ እና ለሱዳን የተሰጠዉ ለምና ዉሃ ቀመስ መሬት እንዲመለስ የሚሉ ቀዳሚ መፈክሮችን ከህዝባችን ጋር አንግቦ ህዝባዊ እንቅስቃሴዉን በማገዝ ጎህ ከፍተኛ ሚና ተጫዉቷል።
