top of page

የጎንደር ሕብረት (ጎሕ) አላማው ምንድን ነው?

  • የክፍለሀገሩን ተወላጆች ያሰባሰበ፤ ለህዝቡ ደህንነትና ታሪካዊ አንድነት ጠበቃ ሆኖ የሚከራከር

  • በአጠቃላይ በኢትዮጵያ እና በተለይ በጎንደር ክፍለሀገር፤  የሰፈነው የዘር 
    ሥርዓት ተወግዶ፣ ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፍትህ እንዲሰፍን አጋር ሆኖ የሚታገል ድርጅት ነው።

 

የጎንደር ሕብረት ተግባር ምንን ያካትታል? 

  • በመላው አለም የሚገኙ የጎንደር ክፍለሀገር ተወላጆችን ማደራጀት።

  • የድርጅቱ ልሳን የሚሆን መፅሄት ማዘጋጀት።

  • የሚሰራውን ግፍ የውጭ ሰባአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች እንዲያውቁት 
    ማድረግ።

  • በዓለም ደረጃ ዘረኛውንና ተስፋፊውን መንግስት ምንነት/ማንነት ማጋለጥ።

  • የፕሮፖጋንዳ ስራዎችን ማካሄድ። 

  • የመረጃ ማሰባሰብ ስራዎችን ማከናወን።

  • በአጠቃላይ በሀገራችን በተለይ በክፍለሀገራችን ለፍትህ የሚደረገውን ትግል
     ድጋፍ መስጠት።

  • የተፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ለሽምግልና የሚሆኑ ሰዎችን ማግኘትና ጥረት 
    ማድረግ።

  • የድርጅቱ ዘላቂ፣ አሰራር እና አወቃቀር በሂደት ማሻሻል።

መግቢያ

የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ወይም ጎህ በዲያስፖራ የሚኖሩ የጎንደር ክፍለህገር ተወላጆች ጥረት በበጎ አድራጎት ስም የተቋቋመ ድርጅት ነው። ጎህ የተቋቋመበት አበይት ምክኒያቶች ክፍለሀገሩ  ባለፈው ክ/ዘመን በተለይም ለአለፉት 40 ና 50 ዓመታት የጦረነት ቀጠና በመሆኑ ምክንያት ልጆች ያለአባት ያደጉበት፣ ሚስት ያለባል የኖረችበት፣ እናትና አባት ያለጧሪ እድሜያቸውን የገፉበት እንዲሁም የመሰረተ ልማት ተጠቃሚ ያልሆነ ክ/ሐገር በመሆኑ ነው።

 

በተለይም ህወሀት (ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ) የአማራውን ህዝብ እንደጠላት ከፈረጀና ወደ ጦርነት ከገባ በኃላ ስላማዊውን ህዝብ እየዘረፈ፣እየገረፈ፣እየሰወረና እየገደለ ለም መሬቱን ለመቀማት ሲል

  1. ትልቁን የልማት ሀገር ወልቃይት፣ ጠገዴን፤ ሁመራና ጠለምትን ለጊዜው ባገኘው ጎልበት ተመክቶ ወደ ትግራይ በመከለልና የራሴ የሚለውን የትግራይ ክ/ሐገርን ተወላጅ አምጥቶ በማስፈር የዘር ማፅዳት ወንጀል በማካሄዱ።

  2.  የጎንደርን ህዝብ አንድነት ለመሸርሸርና ህዝቡ በተወሰደው መሬት ላይ ጥያቄ ማንሳቱን ባለማቋረጡ የህዝቡን አቅጣጫ ለማሳት በሚል ተንኮል ለብዙ ሺ ዘመናት ተከባብሮ፣ተጎራብቶ፣ተዛምዶና ተዋልዶ፤ ድንበር ሳይኖረው አካባቢውን አውቆና አክብሮ የኖረውን የጎንደርን ህዝብ አማራ እና ቅማንት ብሎ ለመከፋፈል የቀየሰውን እኩይ ተንኮል ለማክሸፍ

  3. የጎንደርን መሬት ለሱዳን የእጅ መንሻ አድሩጎ በመስጠቱ ምክኒያትና በሌሎች ዘርፈ ብዙ የክ/ሐገሩ ችግሮች ምክኒያት ጎህ እንዲቋቋም ሆነ።

 ታሪክ እንደሚመሰክረው ጎንደር ክ/ሐገር ገዥዎች በተፈራረቁበት ጊዜ ሁሉ ለስልጣናቸው አደጋ ይሆናል ብለው የሚፈሩትና የሚጠረጥሩት አካባቢ እንደመሆኑ ከማንኛውም የመሰረተ ልማት ተጠቃሚነት ወደ ኃላ ሲጎትቱት በአንፃሩ ደግሞ ኢትዮጵያ ሰላሟ ሲናጋና የህልውና አደጋ ሲገጠማት በግምባር ቀድምትነት የሚጋፈጠው ይህው መከረኛ ህዝብና አካባቢ ነው።  

 

ስለሆነም ህዝቡ አሁን የደረሰበት የኑሮና የእድገት ደረጃ ከሌሎች የሀገሪቱ ክፍል የከፋ ሆኖ እናገኘዋለን።ከላይ በተጠቀሱትና በሌሎች ችግሮች በተለይም በጦርነት ምክኒያት ከሀገሩ የተሰደደው የክ/ሐገሩ ተወላጅ አሁን ከሚገኝበት የተለያየ የዓለም ክፍል ወደ ሀገሩ ተመልሶ ሲሄድ የሚያረጋግጠውም የችግሩን ክፋት፣ስፋትና ጥልቀት በመሆኑ ለዚህ ችግር መፍትሄ ለማፈላለግ የተሰባሰበ ዜጋ ነው። 

 

ስለዚህ ይህን ችግር ከስሩ ለመንቀል ሲባል ጎህ በክ/ሀገሩ የሚካሄደውን የኢኮኖሚ፣ የማህብራዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴን በማገዝ የራሱን ተፅእኖ ለመፍጠር የተመሰረተ ደርጅት ነው።ምንም እንኳን ቀጥተኛ የፖለቲካ ተሳትፎ ባያደርግም የሀገራችን የፖለቲካ ሂደትና መንግስት የሚከተለውን ውሳኔ ግን የክ/ሐገሩን ህዝብ ዳግም ለችግርና ለሰቆቃ እንዳይዳርገው በትጋትና በንቃት የሚከታተል ይሆናል። ክ/ሐገሩ ታሪካዊ ድንበሩ ተጠብቆ፣ ማንነቱ ተከብሮ፣ በሀብቱ ተጠቃሚ ሆኖ ወደ ኃላ የቀረውን የመሰረት ልማት ዝርጋታ ተሻሽሎ በአጠቃላይ የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ይሰራል።ጎንድረ ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት የሚታገልለት አብይ ዓላማውም ይህ ነው።

  • s-facebook
  • Twitter Metallic
  • s-linkedin
bottom of page