






ለጎሕ ማዕከል ይለግሱ
ለጎሕ ማዕከል ይለግሱ
ለማኅበረሰባችን ዘላቂ ማዕከል እንገንባ
ጎሕ ማዕከል በጎንደር፣ ኢትዮጵያ የሚገነባ ቋሚ የማኅበረሰብ፣ የባህል፣ የትምህርትና የልማት ማዕከል ነው። በጎንደር አኩሪ ታሪክና የሥነ ሕንፃ ቅርስ ተነሳስቶ የሚገነባው ይህ ማዕከል፣ ትውልዶችን የሚያገናኝ፣ በውጭ የሚኖሩ ወገኖችን ከአገር ቤት የሚያስተሳስርና ለጎንደርና ለአካባቢው ሕዝብ ዘላቂ ዕድሎችን የሚፈጥር ይሆናል።
የእርስዎ ልገሳ የጎሕ ማዕከልን ዕቅድ፣ ግንባታ፣ ቁሳቁስ ማሟላትና የፕሮግራም ልማት ለመደገፍ ይውላል።
የእርስዎ ልገሳ የሚደግፋቸው አገልግሎቶች
-
አጼ ቴዎድሮስ አዳራሽ
-
የትምህርትና የሥልጠና ክፍሎች
-
ቤተ መጻሕፍትና የምርምር ማዕከል
-
ቤተ መዘክርና የባህል ቅርስ ክፍሎች
-
የጤናና የማኅበራዊ ድጋፍ አገልግሎቶች
-
የወጣቶች ልማት ፕሮግራሞች
-
የቴክኖሎጂና የዲጂታል አገልግሎት ተቋማት
-
የጎሕ ቢሮዎችና የማኅበረሰብ መሰብሰቢያ ቦታዎች
-
የሕዝብ መሰብሰቢያና አረንጓዴ ቦታዎች
የእርስዎ አስተዋጽኦ ትልቅ ለውጥ ያመጣል
እያንዳንዱ ልገሳ—ትልቅም ሆነ ትንሽ—የጎሕ ማዕከልን ወደ እውነታ አንድ ደረጃ ያቀርበዋል። የእርስዎ ድጋፍ የጋራ ራዕያችንን ማኅበረሰቡን ለትውልድ ወደሚያገለግል ቋሚ ተቋም ለመለወጥ ይረዳል።
የአንድ ጊዜ ልገሳ ማድረግ ወይም ወርሃዊ ደጋፊ መሆን ይችላሉ። ሰዎች የሚማሩበት፣ የሚገናኙበት፣ ቅርሳቸውን የሚጠብቁበትና የተሻለ የጋራ የወደፊት ዕድል የሚገነቡበትን ማዕከል በአንድነት እንገንባ።

የዚህ ታሪካዊ ፕሮጀክት አካል ይሁኑ
ጎሕ ማዕከል የሁላችንም ነው። የጎሕ አባላት፣ ጎንደሬዎች፣ የጎንደር ወዳጆች፣ የማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ የንግድ ተቋማትና በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ደጋፊዎች በዚህ ታላቅ ፕሮጀክት እንዲሳተፉ እንጋብዛለን።
የጋራ ቅርስ!
ዛሬውኑ ይለግሱ፤
ጎሕ ማዕከልን በአንድ አስተዋጽኦ፣ በአንድ ማኅበረሰብና በአንድ የጋራ ራዕይ እንገንባ።
የአስራት በኩራት ስፖንሰሮች — 1,000 ዶላርና ከዚያ በላይለጎሕ ማዕከል 1,000 ዶላርና ከዚያ በላይ የሚለግሱ ግለሰቦች፣ ቤተሰቦች፣ ድርጅቶችና የንግድ ተቋማት፣ የአስራት በኩራት ስፖንሰሮች በመሆን ዕውቅና ይሰጣቸዋል።
የሚያደርጉት የላቀ አስተዋጽኦና ቁርጠኝነት የጎሕ ማዕከል ዘላቂ ታሪክ አካል ሆኖ ይመዘገባል። የአስራት በኩራት ስፖንሰሮች በጎሕ ማዕከል በተገቢ የማዕከሉ ቋሚ የዕውቅና ማሳያዎችና በተያያዥ ዝግጅቶች የማዕከሉ ስፖምሰር ሆነው ልዩ ዕውቅና ያገኛሉ።
1,000 ዶላርና ከዚያ በላይ በመለገስ የአስራት በኩራት ስፖንሰር ይሁኑ፤ ለመጪው ትውልድ የሚተላለፍ ዘላቂ አሻራ እንዲገነባ ያግዙ።የልገሳ አዝራሮችአሁን ይለግሱየአስራት በኩራት ስፖንሰር ይሁኑ፡፡
ጎንደር ሕብረት (ጎሕ) በአሜሪካ የውስጥ ገቢ ሕግ ክፍል 501(c)(3) መሠረት የተመዘገበ ትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው። ልገሳዎች በሕግ በተፈቀደው መጠን ከግብር ተቀናሽ ይሆናሉ