top of page

WELCOME

Welcome visitors to your site with a short, engaging introduction. Double click to edit and add your own text.

 

 

 

 

 

 

 

 

 

  gonderhibret.org  gonderhibret72@gmail.com

 

  4126 Deerwood Trail, Eagan MN 55122 

 

               የምስጋና ደብዳቤ

የካቲት 5, 2013

 

ከጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት

አሜሪካ

 

በጀርመን የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ማህበር፣

 ትሕነግ(ወያኔ) በከፈተው የእብሪት ጦርነት ምክንያት ወደ ግንባር ሄደው ለሚዋደቁ የአማራ ልዩ ሃይል፣ ፋኖ/ሚሊሺያና የአገራችን መከላከያ ሃይል እንዲሁም የጦርነቱ ሰለባ ለሆኑት ወገኖቻችን  የእርዳታ ማሰባሰብ ዘመቻ ለተሳተፋችሁ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ላደረጋችሁልን ወገናዊ ርብርብ ፈጣሪ እንዲከፍላችሁ እየተመኘን ልባዊ አድናቆታችንና ምስጋናችን እናቀርባለን።

የጀርመን ጎንደር ሕብረት $7000  (ሰባት ሺ የአሜሪካ ዶላር) ከናንተ ከውድ የኢትዮጵያ ልጆች አሰባስቦ የላከልን መሆኑን እታች አባሪ ባደረግነው መረጃችን

ስናሳውቃችሁ በታላቅ ክብርና ምስጋና ነው።

 

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅ

የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ከ124,400 ብር በላይ የፈጀ የአልባሳትና የምግብ እህል ቁሳቁሶችን ድጋፍ  አደረገ።

 

25/05/2013ዓ.ም የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት 

 

-አብራሃጅራ

 

ድጋፉ በኢትዮ ሱዳን የድንበር ግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉ የሰላም በር ቀበሌ ነዋሪዎች ሲሆን ማህበሩ በባህር ማዶ የሚኖሩ የጎንደር አካባቢ ተወላጆች የተመሰረተ መሆኑንና አካባቢውን ብሎም ሀገር በሰላሙ፣ በልማቱ እንዲሁም በተለያዩ አካባቢንና ሀገርን በሚጠቅሙ የልማት እንቅስቃሴዎች ድጋፍ የማድረግ ዓላማ አድርጎ እየተቀሳቀሰ መሆኑን የሀገር ውስጥ የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ሰብሳቢ አቶ አምላኩ ነጋሽ ተናግረዋል።

 

መህበሩ ከዝህ ቀደም በአብራሃጅራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በሱዳን ጠረፍ ዳር ሲኖሩ የነበሩ 1700 በላይ ነዋሪዎች 4000 ኪሎግራም ማሽላ፣ 160 ብርድ ልብስና 320 ሊትር ዘይት ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀው ማህበሩ የተቸገሩን ለመረዳት ቀጣይነት ባለው መልኩ እንደሚሰራም አቶ አምላኩ አክለው ገልፀዋል።

 

የሰላም በር ተፈናቃይ ወጣት ብርቁ ማሞ ሴቶች፣ ህፃናትና የሀገር ሽማግሌዎች ያሉበት መፈናቀል የከፋ ቢሆንም በመንግሥት ፣ በማህበርና በግለሰብ ደረጃ ለሚደረግልን ድጋፍ ወደ ነበርንበት ቀያችን ለመመለስ ለሚፈጀው ጊዜ በትዕግስት በትጋት እንድንጠብቅ አድርጎናል ብለዋል።

 

የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ብርቱካን ጥጋቡ በበኩላቸው ከክልል ምግብ ዋስትና ቀጥሎ ቀይ መስቀልንና የተለያዩ ባላሃብት ግለሰቦች ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ተናግረው የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ላደረገው ልክ የሌለው ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋናቸውን በተቋሙና በአስተዳደር ምክርቤት ስም  አቅርበዋል።

 

በመጨረሻም የኢትዮ ሱዳን የደንበር ግጭት ስምምነት እስኪደርስ ለተፈናቃዮች አስፈላጊውን እርዳታ እያደረጉ እንደሚቆዩም ወ/ሮ ብርቱካን አክለው ገልፀዋል።

 

በሰለሞን አለምነህ

all and narrow letters, that works well on almost every site.

Central Gondar Communication

Yesterday at 2:10 AM  · 

የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ግምታቸው ከሩብ ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የተለያዩ መድሃኒቶችን ለሳንጃ ፣ለአብርሃጅራና ለሁመራ ሆፒታሎች አስረክቧል፡፡

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ህዳር 19/2013 ዓ/ም (ጎንደር)

የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት በግንባር ለሚገኘው የሃገር መከላከያ ሰራዊት ፣ለአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሽያ አባላት ለህክምና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ መድሃኒቶችን ለሳንጃ ፣ለአብርሃጅራና ለሁመራ ሆፒታሎች አስረክቧል፡፡

የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት የጎንደር ተወካይ አቶ አምላኩ ነጋሽ መድሃኒቶቹን ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት የኢትዮጵያ መንግስት በከሃዲው የህወሃት ጁንታ ላይ እየወሰደ ያለውን ህግን የማስከበር ተልእኮ ለመደገፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

መድሃኒቶቹ በጤና ተቋማቱ ይበልጥ ተፈላጊ መሆናቸውን ያስታወቁት ተወካዩ በቀጣይም መንግስት ህግን ለማስከበር እየወሰደ ያለውን እርምጃ ለመደገፍ ተጨማሪ ድጋፍ ለማድረግ መወሰናቸውን ገልፀዋል፡፡

የሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የፋርማሲ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሙሉቀን ፈረደ ከጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት የተበረከቱት መድሃኒቶች በሆስፒታላችን በስፋት ጥቅም ላይ የሚውሉ በመሆናቸው አስፈላጊነታቸው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

መድሃኒቶቹ በግንባር እየተዋጋ ለሚገኘው የሃገር መከላከያ፣ ለአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሽያ አባላት አገልግሎት እንዲውሉ አስፈላጊው ሁሉ እንደሚደረግ አብራርተዋል፡፡

ንጋቱ የሱፍ

goh2.png

Central Gondar Communication

November 13 at 2:25 AM  · 

የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት የግማሽ ሚሊዮን ብር የመጀመሪያ ዙር ድጋፍ አደረገ

ጥቅምት 04/2013 የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ

የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት የግማሽ ሚሊዮን ብር የመጀመሪያ ዙር ድጋፍ አደረገ

የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ማህበር ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ለአማራ ልዩ ሀይልና ለሚሊሻ አባላት የግማሽ ሚሊዮን ብር የመጀመሪያ ዙር ድጋፍ ማድረጋቸውን የማህበሩ ተወካይ የሆኑት አቶ አምላኩ ነጋሽ ተናግረዋል፡፡

አቶ አምላኩ ነጋሽ አክለውም ድጋፉ የተሰበሰበው አሜሪካን አገር ከሚኖሩ የጎንደር አካባቢ ተወላጆች ሲሆን መንግስት የጀመረውን ህግ የማስከበር ስራ እንደሚደግፉና በቀጣይም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡

የጎንደር ቀጠና ሎጅስቲክ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ባንቲሁን መኮነን በበኩላቸው አሁን ላይ በየደረጃው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በርካታ ድጋፎችን እያደረጉ እንደሚገኙ ገልፀው በዛሬው እለትም የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ማህበር የ500 ሽ ብር ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

አቶ ባንቲሁን አክለውም የጎንደር ህብረት ማህበር ከዚህ በፊት አካባቢው ላይ ተፈጥረው በነበሩ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ምክንያቶች ማህበሩ በርካታ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው አሁን ላይም ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ከአማራ ልዩ ሀይልና የሚሊሻ አባላት ጎን መሆናቸውን አሳይተዋል ብለዋል፡

122367239_1708565522646278_2435161041255

Central Gondar Communication

10h  · 

በሰሜን አሜሪካና ጀርመን ሀገር ከሚኖሩ የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት እንዲሁም የጎንደር ልማት ማህበር የአንድ መቶ ኩንታል በቆሎ ድጋፍ አደረጉ።

ጥቅምት 12/2013 የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ

በሰሜን አሜሪካና ጀርመን ሀገር ከሚኖሩ የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት እንዲሁም የጎንደር ልማት ማህበር የመቶ ኩንታል በቆሎ ድጋፍ ማድረጋቸውን የህብረቱ ተወካይ የሆኑት አቶ አምላኩ ነጋሽ ተናግረዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ ደንቢያ በጎርፍ ለተፈናቀሉ ወገኖች መሆኑን አስረድተዋል።

አቶ አምላኩ ነጋሽ ጨምረው አንደገለፁት ህብረቱ የወገን ደራሽነቱን ያሳየበት ተግባር ሲሆን በዚህ በያዝነው ወር በተመሳሳይ መልኩ ለደቡብ ጎንደር ዞን በጎርፍ ለተፈናቀሉ ወገኖች 176 ኩንታል ድጋፍ ማድረጋቸውን አብራርተዋል።

በርክክብ ስነ-ስርዓቱ የተገኙት የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ተወካይ አቶ እምቢአለ ታረቀኝ በበኩላቸው ለወገን ደራሽ ወገን ነውና የተሰጠውን እርዳታ በተፈናቃዮች ስም ከልብ እያመሰገን ሌሎች ወገኖችም አስፈላጊውን ድጋፍ እንድታደርጉልን ጥሪያችን እናቀርባለን ብለዋል።

የጎንደር ህብረት ከአሁን በፊት በጭልጋና አካባቢው በተፈጠረው ግጭት ለተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ ማድረጋቸውን አቶ እምቢአለ ታረቀኝ አንስተው ድርጅቱ ሁሌም ከጎናች መሆኑን አሳይቶናል ብለዋል።

በዋኘው አዳነ

122167752_1708565915979572_2111464096612

South Gondar Zone Communication

October 15 at 2:42 PM  · 

በደቡብ ጎንደር እስተዳደር ዞን በፎገራ፣ ሊቦ እና ደራ ወረዳወች በጣና ወደኋላ መመለስ መክንያት ጉዳት ለደረሰባቸውን አርሶ አደሮች 176.7 ኩንታል በቆሎ ድጋፍ ተደረገላቸው፡፡

የደቡብ ጎንደር እስተዳደር ዞን አደጋ መከላከልእና ምግብዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አገኘሁ ዳኛው በሶስቱ ወረዳወች በ7 ቀበሌወች በጣና ወደኋላ መመለስ ምክንያት ከመኖሪያ አካባቢያቸው ለተፈናቀሉ አርሶ አደሮች ከተለያዩ ረጅ ድርጅቶች፣ማህበራት እና ባለሃብቶች ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ ጠቁመው በእለቱ ከስሜን አሜሪካ እና በጀርመን አገር የሚኖሩ የጎንደር ህብረት እና የጎንደር መልሶ ማቋቋምና ልማት ማህበር አባላት 176.7 ኩንታል በቆሎ ድጋፍ መደረጉን አስመልክቶ በዞኑ ተጎጅ አርሶ አደሮች ስም የላቀ ምስጋና አቅርበዋል ፡፡

አቶ አገኘሁ አክለውም እነዚህን አርሶ አደሮች በዘላቂነት ለማቋቋም ውሃው እየሸሸ ሲሄድ የተለቀቀውን ማሳ በተተኪ ዘር እየሸፈኑ ምርት እንዲያመርቱ አሁን ላይ ሰፊ የሆነ ቅንጅታዊ ስራ የሚጠይቀው ከ 8ሽህ 500 ኩንታል በላይ ተተኪ ዘር በተገቢው መንገድ እንዲቀርብ ማድረግ ነው፡፡ከዚህ ጎን ለጎን እንደ የውሃ ፣ትምህርት፣ ጤና እና መሰል ተቋማት እንዲሟሉ በማድረግ ወደ ቀያቸው የመመለስ ስራ በቅንጀት መስራት እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የደቡብ ጎንደር መልሶ ማቋቋምና ልማት ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ሞላ እንግዳ በእርክክቡ ላይ ተገኝተው ማህበሩ በስሜን አሜሪካ እና በጀርመን አገር የሚኖሩ የጎንደር ህብረት ማህበር ጋር በመቀናጀት ከዚህ ቀደም የኮሮና ውረርሽኝን ለመከላከል ለ5ቱ ዞኖች 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት ዘይት እና የፊኖ ዱቄት ድጋፍ እንዳደረገ ጠቁመው በእለቱ 176.7 ኩንታል በቆሎ በጎንደር ከተማ የጎንደር ህበረት ኮሚቴ ጸሀፊ ከወጣት ምህረት አምሳሉ እና ሆነልኝ አበበ ጋር አስረክበዋል፡፡

ወጣት ምህረት አምሳሉ እና ሆነልኝ አበበ ማህበሩ ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢወች እለታዊ ድጋፍ የማድረግ ስራ ሲሰራ እንደቆየ ጠቁመው በቀጣይ መሰረቱን ጎንደር ላይ በማድረግ አገር በቀል መንግስታዊ ያለሆነ ተቋም ሁኖ በዞኑ ያሉ ችግሮችን በመለየት ችግር ፈች በሆኑ መሰረተ ልማቶች ላይ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

በእርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አወቀ ዘመነ የጎንደር ህብረት በአሜሪካ እና ጀርመን አገር የሚኖሩ ተወላጆች ከዚህ በፊት የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ከ300 ሽህ ብር በላይ ወጭ በማድረግ 300 ኩንታል ፊኖ ዱቄት እና 517 ሊትር ዘይት ለችግር ለተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡

እንዲሁም የእርብ እና የጉማራ ወንዞች የክረምት የጎርፍ ውሀ የመሸከም አቅማቸው እንዲያድግ ዞኑና የክልሉ መንግስት በቅንጅት ባደረገው ጥረት ውጤት ያስገኘ እንደሆነ ጠቁመው የጣናን ወደኋላ መመለስ ተከትሎ በደራ ፣ፎገራ እና ሊቦ ከምከም ወረዳዎች ጉዳት የደረሰ በመሆኑ ህብረተሰቡን ለማገዝ በሚደረገው ጥረት ገንዘብ በማሰባሰብ በ220 ሽህ 885 ብር 176.7 ኩንታል ለምግብነት የሚውል በቆሎ በዛሬው እለት አስረክበውናል፡፡ በመሆኑም ድጋፉን ላደረሱት እና ገንዘቡን ለለገሱ ሁሉ በዞኑ ስም የላቀ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት

ጥቅምት 06/2013 ዓ/ም

ዘጋቢ፣ምህረት አለሙ

October 22, 2020

Aid to S Gonder.png

ጎንደር ሕብረት በጎርፍ ለተጎዱ እርዳታ ላክ

​መስከረም 25፣ 2020

ጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ስሜን አሜሪካና ጀርመን በጎርፍ የተነሳ ክብቶቻቸው በጎርፍ ለተወስዱያ፤ ንብረታቸው ፤ስብላቸውንና ቤቶቻቸው በውሀ ለተጥለቀለቁ  የደራ፤ ፎገራ ፤ሊቦ ክምከም እንዲሁም ደንቢያ ወረዳዎቸ የገንዝብ ማሰባሰብ ካካሄደ በኋል $10000 ( 350 000 ብር ልኳል፡ ፡የምጋብ  እርዳታ ስርጭቱን  የጎንደር ቻፕተር በጎንደር ከተማ ክጎልማና  ክአደጋ መክላከልና የምግብ አቅርቦት ተወካዮች ጋር  በመተባበር በደራ፤ሊቦ ክምክምና ፎገራ ወረዳዎችያብረከተ ሲሆን በቅርቡ ደጎሞ እርዳታውን ለደንቢያ ወረዳ ያበርክታል፡፡ 

Thank you for your generous support. Our ability to proomot economic  and  soical justice in  Ethiopia depends  on your support. 
 

Please support Gonder Hibret

  • Facebook Classic
  • Twitter Classic
  • Google Classic

ሰላም  ሁኝ ጎንደር፣ ታምራት ሞላ

bottom of page