የወያኔ መንግስት የሰሜን ጎንደር ዞንን ለመከፋፈልና የምዕራብ ጎንደርን መሬት ለመቀራመት ያወጣዉ እኩይ እቅድ አገር አጥፊ ነው!
በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን እንድምንሰማዉ የወያኔ አስተዳደር የሰሜን ጎንደር ዞንን ለሶስት ለመክፈል እንደወሰነና ለዚህም ምክንያቱ ላለፉት 26 አመታት ለልማት ምቹ ስላልሆነ ነው የሚል ነዉ። የአማራን መሬቶች የትግራይ ለማድረግ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአማራና ቅማንት ማኅበረሰብ ተቀላቅለው በሚኖሩባቸው 12 ቀበሌዎች ሕዝበ ውሳኔ ለማካሄድ እየተዘጋጀ ነውም ተብሏል። ይባስ ተብሎ የ“ታላቋ ትግራይን” ሕልም ለመተግበር ሕወሃቶች ጎንደርና ጎጃም ከሱዳን እንዳይዋሰኑ ለማድረግ ትግራይን እስከ ጋምቤላ ለማስፋፋት ያዘጋጁት ሚሥጥራዊ ካርታ በቅርቡ ይፋ ወጥቶ ለማየት በቅተናል
