






ለጎሕ ማዕከል ይለግሱ
የጎንደር ሕብረት (ጎሕ) በ2014 ዓ.ም. የተመሠረተ፣ በአሜሪካ የ501(c)(3) የበጎ አድራጎት ድርጅት ሆኖ የተመዘገበ፣ የጎንደርን ታሪክ፣ ባህል፣ ማኅበራዊ አንድነትና ልማት ለማጠናከር የሚሠራ ተቋም ነው።
ከተመሠረተ ወዲህ የድርጅቱ እድገትና አቅጣጫ በአባላት ተሳትፎ በተካሄዱ ሦስት ጉባኤዎች ተመርቷል፤ የመጀመሪያው ጉባኤ በ2016፣ ሁለተኛው ጉባኤ በ2018፣ ሦስተኛው ጉባኤ ደግሞ በግንቦት 2025 ተካሂደው የድርጅቱን ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ የውስጥ ደንብ፣ የስትራቴጂ ዕቅድና የተቋማዊ እድገት አቅጣጫ አጽድቀዋል።
በጎሕ የውስጥ ደንብ መሠረት ጉባኤው የድርጅቱ ከፍተኛ የውሳኔ ሰጪ አካል ሲሆን፣ ቦርዱ ጉባኤውን በመወከል በጉባኤው የጸደቁትን ፖሊሲዎችና አቅጣጫዎች የማስፈጸም፣ የድርጅቱን ሀብትና ፕሮጀክቶች የመቆጣጠር እና አስፈላጊ ውሳኔዎችን የማሳለፍ ኃላፊነት አለበት።
በሦስተኛው የጎሕ ጉባኤ በተሰጠው የስትራቴጂ አቅጣጫ መሠረት፣ ጎሕ በጎንደር ከተማ ቋሚ የጎሕ ማዕከል በመገንባት ለትምህርት፣ ለባህል፣ ለማኅበራዊ አገልግሎት፣ ለምርምር፣ ለወጣቶችና ለማኅበረሰብ ልማት የሚያገለግል ዘላቂ ተቋም የመመሥረት ሥራ ተጀምሯል።
ቀጣዩ አራተኛው የጎሕ ጉባኤ በግንቦት 2028 በጎንደር ከተማ በጎሕ አዳራሽ (GOH Center Events Hall) እንዲካሄድ በድርጅቱ የረጅም ጊዜ ዕቅድ ውስጥ ተካትቷል። ይህም የጎሕ ማዕከል ፕሮጀክት የድርጅቱ ቀጣይ ትውልድ የሚጠቀምበት ቋሚ ተቋም መሆኑን ያሳያል።
በዚህ መሠረት፣ ቦርዱ የጎሕ ማዕከል ፕሮጀክትን በሙሉ በመመርመር፣ የሕንፃ ንድፉን፣ በደረጃ የሚከናወነውን የግንባታ ዕቅድ፣ የፋይናንስ ስልቱን፣ የአስተዳደር መዋቅሩንና የሥራ አፈጻጸሙን በማጽደቅ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል።
የጎሕ ማዕከል (ብርሃን ማዕከል) በጎንደር ከተማ ለመገንባት የታቀደ፣ የጎንደርን ሕዝብና በዓለም ዙሪያ የሚገኘውን ዲያስፖራ የሚያገናኝ ሁለገብ የማኅበረሰብ ማዕከል ነው። ራዕዩ ትውልድን በዕውቀትና በትብብር ማብቃት፣ ባህልና ታሪክን መጠበቅ፣ ማኅበራዊ አንድነትን ማጠናከር እና ዘላቂ ልማትን ማፋጠን ነው።
ማዕከሉ የትምህርትና የሙያ ሥልጠና፣ የቤተመጻሕፍትና ምርምር፣ የጤናና ማኅበራዊ ድጋፍ፣ የወጣቶችና ቤተሰብ ማበልጸጊያ፣ የባህልና ቅርስ ጥበቃ፣ የቴክኖሎጂና ዲጂታል ተደራሽነት፣ የንግድና ሥራ ፈጠራ፣ የሕዝብ ውይይትና ሰላም እንዲሁም የዲያስፖራ ትስስር አገልግሎቶችን ያቀርባል። የ500 ሰዎች መቀመጫ ያለው አጼ ቴዎድሮስ አዳራሽም ለስብሰባዎች፣ ለባህላዊ ዝግጅቶችና ለማኅበረሰብ መርሐ ግብሮች ያገለግላል።
ብርሃን ሰፈር — ዕውቀት፣ ባህል፣ አንድነትና ልማት የሚገናኙበት የተስፋ ማዕከል!
ጽንሰሀሳብ፤ የፋሲለደስ ትውፊት፣ የእቴጌ ጥይቱ አርበኝነት፣ ቴዎድሮስ አዳራሽ፣ እቴጌ ምንትዋብ እውቀት በር፣ ሀኪም ወርቅነህ ጤና በር፣ ልዑል አለማየሁ ቤተ መጽሀፍት፣ ፋሲለደስ ቤተመዘክር፣ በአጭር ቢጨመር





የጎሕ ማዕከል — ብርሃን ሰፈር
የጎሕ ማዕከል (ብርሃን ሰፈር) በጎንደር ከተማ ለመገንባት የታቀደ፣ የጎንደርን ሕዝብና በዓለም ዙሪያ የሚገኘውን ዲያስፖራ የሚያገናኝ ሁለገብ የማኅበረሰብ ማዕከል ነው። ራዕዩ ትውልድን በዕውቀትና በትብብር ማብቃት፣ ባህልና ታሪክን መጠበቅ፣ ማኅበራዊ አንድነትን ማጠናከርና ዘላቂ ልማትን ማፋጠን ነው።
የማዕከሉ ጽንሰ ሐሳብ የአፄ ፋሲለደስን የሥነ ሕንፃና የሥልጣኔ ትውፊት እንዲሁም የእቴጌ ጣይቱን አርበኝነት፣ አመራርና የነፃነት መንፈስ የሚያንጸባርቅ ነው። ታሪካዊ ቅርሶችን ከዘመናዊ አገልግሎቶች በማጣመር፣ ያለፈውን ትውልድ ከዛሬውና ከወደፊቱ ጋር ያስተሳስራል።
ጎሕ ማዕከል የመጀመሪያው ደረጃ ግንባታ የሚከተሉትን አገልግሎቶች ያካትታል፡
-
የ500 ሰዎች መቀመጫ ያለውን አፄ ቴዎድሮስ አዳራሽ፣
-
ለትምህርትና ለሙያ ሥልጠና የሚውለውን እቴጌ ምንትዋብ ዕውቀት በር፣
-
የጤናና ደኅንነት አገልግሎት የሚሰጠውን ሐኪም ወርቅነህ ጤና በር፣
-
የንባብና ምርምር ማዕከል የሆነውን ልዑል አለማየሁ ቤተ መጻሕፍት
-
የጎንደርን ታሪክ፣ ባህልና ቅርስ የሚያስተዋውቀውን ፋሲለደስ ቤተ መዘክር ያካትታል።
ብርሃን ሰፈር — ታሪክ፣ ዕውቀት፣ ጤና፣ ባህልና ልማት የሚገናኙበት የትውልድ ተስፋ!