His Holiness Passes

gonderhibret@gmail.com ለኢትዮጵያ አንድነት www.gonderhibret.org
4126 Deerwood Trail, Eagan MN 55122 Tel 651 600 8479
መጋቢት 1 2014 ዓ. ም. (03/10/2022)
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ከ ጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት
በቅድሚያ መንፈሳዊ ሠላምታችን እናቀርባለን፤
በቅርቡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፣ ርዕሰ ሊቃነ ፓፓሳት ዘኢትዮጵያ ከዚህ ዓለም በሞት ስለተለዩን ጥልቅ ሃዘን ተሰምቶናል። ቅዱስነታቸው ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላደረጓቸው አበርክትዎች በሕይወት እያሉ ያከናወኗቸው ሐዋርያዊ ተግባሮች ይመሰክራሉ። ቅዱስነታቸው በአሜሪካም ሆነ ወደ አገራቸው ተመልሰው በነበራቸው የተመስጦ፣ የጾም-የፀሎት፣ የብትውትናና የመናኝ ሕይወት መንፈሳዊ ሕይወት ምን ማለት እንደሆነ ለቤተክርሲቲያናችንና ለምዕመናኑ አስተምረውናል። ፀሎታቸውንና ቡራኬያቸውን ማጣታችን ቢያሳዝነንም በሕይወት እያሉ በተግባር ባስተማሩን መንፈሳዊ ሕይወትና የእምነት ፅናት እየተፅናናን እንሰናበታቸዋለን።
የቅዱስነታቸው ቡራኬ ይድረሰን።
በረከታቸው አይለየን፤
እግዚአብሔር የቤተክርስቲያናችንን አንድነት ይጠብቅ፤
የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት
ግርማ ይስማው፣
የሥራ አስኪያጅ ሊ/መ