top of page

ጥምቀት የአንድነት ምልክት ነው

  • Jan 16
  • 2 min read

ጥምቀት የአንድነት ምልክት ነው።

በመላው ዓለም ለምትገኙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችና ወዳጆች በሙሉ እንኳን ለ2018 ባህረ-ጥምቀት

አደርሳቹህ።


ጥምቀት በኢትዮጵያ በተለይም በጎንደር በዓለም አቀፍ የጥንታዊ መዝገብ ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኝ ሀይማኖታዊ፣ታሪካዊ እና

ባህላዊ እሴታችን ነው። ምንም እንኳን በአሁኑ ወቅት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዩ በሁሉም የሐገሪቱ ክፍል እየተሳደደና በእምነቱ

ምክኒያት እየተገደለ ቢሆንም ክርስትናን ከሰጠን ከባለቤቱ ከጌታችን ከመዳህኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ጀምሮ ክርስትና እየተገፋ የሚበረታ፤

እየተገደለ የሚበዛ፤እየተጠላ የሚወደድ ሐይማኖት በመሆኑ እምነቱ በብዙ ታሪካዊ ሂደት አሁን ካለንበት ጊዜ ደርሷል። አባቶቻችን

እምነታቸውን ጠብቀው የሌላውንም አክብረው ሐገራቸውን ጠብቀው ለዚህ ትውልድ አስረክበዋል። የዘንድሮም ጥምቀት እንደበፊቱ

በመላው ሐገራችን በድምቀት ተከብሮ የሚውል ሲሆን፤ በተለይም በጎንደር ደግሞ እጅግ ማራኪ እና አስደናቂ ክብሩን ጠብቆ እንደሚውል

ተስፋ እናደርጋለን።


ጥምቀት በጎንደር የተለየ የሚያደርገው ከመላው ዓለም ታዳሚዎችን የሚሰብ ሲሆን ከፍተኛ የሆነ የውጭ ሐገር እና የሐገር ውስጥ

ቱሪስት በናፍቆት እና በፍቅር ደጋግመው የሚመጡበት ክብረ በዓል እየሆነ ከመጣ በርካታ ዓመታትን አስቆጥሯል። እናትዋ ጎንደርም

ልጆቿን በዕምነት፣ በጎሳ ሳትለያይ እንግዶቿን ከየመጡበት ተቀብላ አምራ፣ተውባ፣ተሞሽራ የምትጠብቅበት ጊዜ ነው። ጥምቀት በጎንደር፤

ከእምነቱ በተጨማሪ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የእየራሱን ባህል፣ ወጉን፣ አለባበሱን፣ ጭፈራውን ሐገር አፍቀሪነቱን የሚያሳይበት ድንቅ በዓል

ነው። ጎንደር በጥምቀት የሄደ ሰው የጎንደሬን ከሰው ጋር አብሮ መኖር ፣ መብላት መጠጣት፣ እንግዳ ተቀባይነቱን የሚረዳበትና

በመስተንግዶው የሚደነቅበት ሲሆን ጎንደሬና ጎንደር ሁሌም በናፍቆት የሚጠብቁት ቀን እና ወራት ነው።


ጥምቀት ጌታችን መዳህኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በየርዳኖስ ወንዝ ሲጠመቅ አንድነቱን እና ሦስትነትን የገለጠበት አንድ የመሆን

ሚስጥሩን ያሳየበት ነው። ጥምቀትን በጎንደር በምናከብርበት ጊዜ ከመላው ዓለም የተሰበሰበ የሰው ዘር በሙሉ ዘሩን፣ ዕምነቱን፣ ቋንቋውን

ሳይለይ ሰው በመሆኑ ብቻ ተገናኝቶ አማኙ ዕምነቱን ፤ የማያምንበትም ትርኢቱን እያየ ደስ ብሎት የሚውልበት የአንድነት ምልክት

እንደመሆኑ፤ ጎንደሬ እርስ በራሱ በዕምነት፣ በጎሳ፣ በቋንቋና በፖለቲካ ሳይከፋፈል ሰላሙን፣ ልማቱን፣ አንድነቱን እና ፍቅሩን ሊገልጽበት

የሚገባ አጋጣሚ እንዲሆን ጎንደር ህብረት ከፍ ያለ ምኞቱን ይገልጻል።


ይልቁንም የጎንደር ጥምቀት በዓል አከባበር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ፣ እየሰፋ በመምጣቱ በዓሉን በተሳካ እና ባማረ ሁኔት

ይከዎን ዘንድ ፤ ማንኛውም ጎንደሬ ፡ ከመላው ዓለም በዓሉን ለማክበር የሚመጣውን ታዳሚ በሐላፊነት የማስተናገድ እና ደኅንነቱን

የመጠበቅ ግዴታ እንዳለበት በመረዳት የዜግነት ግዴታውን ሊወጣ ይገባዋል። ምክንያቱም ዛሬ ጎንደር ጠላቶቿ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ

እምነቷን፣ ወሰኗን የሚጋፉባት፣ታሪክ እና ክብሯን የሚዳፈሩባት፣ልጆቿን የሚያሳድዱባት፣የሚግድሉባት በአጠቃላይ ማነነቷን ለማራከስ

አውሬ ፤ የሚበላውን ለማደን እንደሚሽምቅበት ፣ እንደሚያደባበት ሁሉ የጎንደር እና የኢትዮጵያ ጠላቶች እያደቡ መሆኑን ማንኛውም

ጎንደሬ በንቃት እና በትዕግስት ሊከታተለው ስለሚገባ ነው። እየተከታተለውም ይገኛል።


ስለሆነም፡ እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን። ታላቁ መጽሐፍ “አባቶችህ ያስቀመጡልህን ድንበር አትለፍ" እንዲል ጎንደሬ የሰው

የማይፈልግ የራሱንም የማይሰጥ ታላቅ ህዝብ እንደመሆኑ ፤ ለድብቅ ዓላማቸው ሲሉ ወሰንን እና ድንበረን ከሚጋፉት ታናናሾች፤

ትንሽነትን አይቀበለም ፤ አይማርም። ጎንደሬ ትንሽነት አይመጥነውምና ፤ አባቶቻችን ትንሽነትን ተጸይፍው ፤ ተበታትና የነበርች

ሐገራችንን አንድ ትለቅ እና ታላቅ ክብር ያላት ፤ ታሪኳን የጠበቀች ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ያልወጡት ተራራ ፤ ያልወረዱት ቁልቁለት

፤ ያላቋረጡት በርሃ አልነበረም። ስለሆነም ጎንደሬነትን ብሎም ኢትዮጵያዊነትን ለማፍረስ ፤ ትንሽነትንና ጠባብነትን እንደ መልካም ነገር

ከአባቶቻቸው ከተረከቡት ጋር ህብረት የለንምና የምንታገላቸው መሆኑን እንዲያውቁት እንላለን። በአንጻሩ የአባቶቻችንን ጀግንነት ፣

ኩራት ፣ አንድነትና ርስት ከሚጠብቁት ፣ ከሚያስመልሱት ፤ የቀደመውን ዝናዋንና ተሪኳን ከሚዘክሩት፤ የሐገር ክብር ተከራካሪዎች ጋር

ደግሞ እንደ ባህረ-ጥምቀት አንድነታችንን የምንገልጽበት፤ የአንድነት አፍቃሪዎች መሆናችንንም ልናረጋግጥ እንወዳለን።


እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ይባርክ።

ጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት


 
 
 

Comments


Featured Posts
Recent Posts
Search By Tags
Follow Us
  • Facebook Classic
  • Twitter Classic
  • Google Classic
david-whipple-mU-wz7JlJMc-unsplash_Ravid.jpg
  • s-facebook
  • Twitter Metallic
  • s-linkedin
bottom of page